Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማቴዎስ 26:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ አንድ ብልቃጥ የአልባስጥሮስ ሽቱ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በማእድ ላይ ተቀምጦ ሳለም በራሱ ላይ አፈሰሰችው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በማዕድም ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በራሱ ላይም አፈሰሰችው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በዚያም ኢየሱስ በማእድ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ሽቶውንም በራሱ ላይ አፈሰሰችው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።

Ver Capítulo Cópia de




ማቴዎስ 26:7
12 Referências Cruzadas  

ነቢ​ዩም ኤል​ሳዕ ከነ​ቢ​ያት ልጆች አን​ዱን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ይህን የዘ​ይት ቀንድ በእ​ጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድም ሂድ።


በሌ​ሊት በቤተ መቅ​ደስ እጆ​ቻ​ች​ሁን አንሡ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ስ​ግ​ኑት።


የሞቱ ዝን​ቦች የተ​ቀ​መ​መ​ውን የዘ​ይት ሽቱ ያገ​ሙ​ታል፤ በስ​ን​ፍ​ናም ካለ ታላቅ ክብር ይልቅ ትንሽ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች።


ሁል​ጊዜ ልብ​ስህ ነጭ ይሁን፤ ቅባ​ትም ከራ​ስህ ላይ አይ​ታጣ።


የሽ​ቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ሽቱ ነው፤ ስለ​ዚህ ደና​ግል ወደ​ዱህ።


ዝሙ​ት​ሽን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አበ​ዛሽ፤ ከአ​ንቺ የራቁ ብዙ​ዎ​ች​ንም ተጐ​ዳ​ኘሽ። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ሽ​ንም ወደ ሩቅ ላክሽ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ተወ​ገ​ድሽ፤ እስከ ሲኦ​ልም ድረስ ተዋ​ረ​ድሽ።


ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቈጡና “ይህ ጥፋት ለምንድር ነው?


እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ የናርዶስ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፤ ብልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።


አንተ ራሴን እንኳ ዘይት አል​ቀ​ባ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን እግ​ሬን ሽቱ ቀባ​ችኝ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios