Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማቴዎስ 26:58 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

58 ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፤ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

58 ነገር ግን ጴጥሮስ ከርቀት ሆኖ እስከ ሊቀ ካህናቱ ቅጥር ግቢ ይከተለው ነበር፤ ወደ ውስጥ ገብቶም የሁኔታውን መጨረሻ ለማየት ከጠባቂዎቹ ጋራ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

58 ጴጥሮስም እስከ ሊቀ ካህኑ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፤ የነገሩንም ፍጻሜ ለማየት ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

58 ጴጥሮስ ግን እስከ ካህናት አለቃው ግቢ ድረስ ኢየሱስን በሩቅ ተከተለው፤ ወደ ውስጥ ገብቶም የነገሩን ፍጻሜ ለማየት ከዘበኞች ጋር ተቀመጠ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

58 ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፥ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ።

Ver Capítulo Cópia de




ማቴዎስ 26:58
10 Referências Cruzadas  

በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፤


አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፤ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤


ይዘ​ውም ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ቤት ወሰ​ዱት፤ ጴጥ​ሮ​ስም ከሩቅ ይከ​ተ​ለው ነበር።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፤ “አን​ተስ ከእ​ርሱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ወገን አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ ካደ።


ሊቃነ ካህ​ና​ትና ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ባዩት ጊዜ፥ “ስቀ​ለው! ስቀ​ለው!” እያሉ ጮሁ፤ ጲላ​ጦ​ስም፥ “እና​ንተ ራሳ​ችሁ ውሰ​ዱና ስቀ​ሉት፤ እኔስ በእ​ርሱ ላይ በደል አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም” አላ​ቸው።


ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ሕዝቡ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት እንደ አጕ​ረ​መ​ረሙ ሰሙ፤ የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይይ​ዙት ዘንድ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ላኩ።


ሎሌ​ዎ​ቹም ወደ ካህ​ናት አለ​ቆ​ችና ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ተመ​ለሱ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ያላ​መ​ጣ​ች​ሁት ለም​ን​ድን ነው?” አሉ​አ​ቸው።


አሽ​ከ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም መጥ​ተው በወ​ኅኒ ቤት አጡ​አ​ቸ​ውና ተመ​ል​ሰው ነገ​ሩ​አ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ የቤተ መቅ​ደሱ ሹም ከሎ​ሌ​ዎቹ ጋር ሔዶ አባ​ብሎ አመ​ጣ​ቸው፤ በግ​ድም አይ​ደ​ለም፤ በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ይ​ደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ሕዝ​ቡን ይፈሩ ነበ​ርና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios