Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማቴዎስ 26:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ “እንግዲህስ ተኙ፤ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች፤ የሰው ልጅም በኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 ከዚያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንም ዐርፋችሁ ተኝታችኋል? እነሆ፤ ሰዓቱ ቀርቧል፤ የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ ዐልፎ ይሰጣል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ከዚህ በኋላ ወደ ደቀመዛሙርቱ መጥቶ እንዲህ አላቸው “ከእንግዲህስ ተኙ፥ ዕረፉም፤ እነሆ ሰዓቱ ቀርቦአል፤ የሰው ልጅም በኀጢአተኞች እጅ ተላልፎ ይሰጣል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ከዚህ በኋላ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ መጣና እንዲህ አላቸው፤ “አሁንም ገና ተኝታችኋልን? ዕረፍትም እያደረጋችሁ ነውን? እነሆ፥ የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ ተላልፎ የሚሰጥበት ሰዓቱ ደርሶአል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ፦ እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች የሰው ልጅም በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።

Ver Capítulo Cópia de




ማቴዎስ 26:45
14 Referências Cruzadas  

በቀ​ት​ርም ጊዜ ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ፥ “አም​ላክ ነውና በታ​ላቅ ቃል ጩኹ፤ ምና​ል​ባት ይጫ​ወት ይሆ​ናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆ​ናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀ​ስ​ቀስ ያስ​ፈ​ል​ገ​ዋል” እያለ ይዘ​ባ​በ​ት​ባ​ቸው ጀመር።


አንተ ጐበዝ፥ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ደስ ይበ​ልህ፥ በጕ​ብ​ዝ​ና​ህም ወራት ልብ​ህን ደስ ይበ​ለው፥ በል​ብ​ህም መን​ገድ፥ ዐይ​ኖ​ች​ህም በሚ​ያ​ዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለ​ዚህ ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ፍርድ እን​ዲ​ያ​መ​ጣህ ዕወቅ።


እርሱም “ወደ ከተማ ከእገሌ ዘንድ ሄዳችሁ ‘መምህር ጊዜዬ ቀርቦአል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ከአንተ ዘንድ ፋሲካን አደርጋለሁ ይላል’ በሉት፤” አለ።


ለደቀ መዛሙርቱ “ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንዲሆን ታውቃላችሁ፤ የሰው ልጅም ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል፤” አለ።


ደግሞም ትቶአቸው ሄደ፤ ሦስተኛም ያንኑ ቃል ደግሞ ጸለየ።


ተነሡ፤ እንሂድ፤ እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል፤” አላቸው።


ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በምድርም ወድቆ፥ ይቻልስ ቢሆን ሰዓቲቱ ከእርሱ እንድታልፍ ጸለየና


ዘወ​ት​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር በቤተ መቅ​ደስ ስኖር እጃ​ች​ሁን እንኳ አል​ዘ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብ​ኝም፤ ነገር ግን ጊዜ​ያ​ችሁ ይህ ነው፤ የጨ​ለ​ማው አበ​ጋ​ዝም ሥል​ጣኑ ይህ ነው።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፤ “አሁን የሰው ልጅ ይከ​ብር ዘንድ ጊዜው ደረሰ።


“አሁ​ንስ ነፍሴ ታወ​ከች፤ ግን ምን እላ​ለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍ​ሴን አድ​ናት፤ ነገር ግን ስለ​ዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደር​ሻ​ለሁ።


ከፋ​ሲካ በዓል አስ​ቀ​ድሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዚህ ዓለም ወደ ላከው ወደ አብ ይሄድ ዘንድ ጊዜው እንደ ደረሰ ባወቀ ጊዜ በዓ​ለም ያሉ​ትን የወ​ደ​ዳ​ቸ​ውን ወገ​ኖ​ቹን ፈጽሞ ወደ​ዳ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ነገር ተና​ግሮ ዐይ​ኖ​ቹን ወደ ሰማይ አነ​ሣና እን​ዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደር​ሶ​አ​ልና ልጅህ ያከ​ብ​ርህ ዘንድ ልጅ​ህን አክ​ብ​ረው፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios