Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማቴዎስ 24:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችሁማል፤ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “በዚያ ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችኋል፤ በስሜ ምክንያት በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋልም፤ ስለ ስሜም በሕዝቦች ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋል፤ ስለ ስሜም በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ማቴዎስ 24:9
26 Referências Cruzadas  

የቀሩትም ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው፤ ገደሉአቸውም።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤


ስለ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበቡ እን​ዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢ​ያ​ት​ንና ሐዋ​ር​ያ​ትን ወደ እነ​ርሱ እል​ካ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ይገ​ድ​ላሉ፤ ያሳ​ድ​ዳ​ሉም።


ከዚ​ህም ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ይይ​ዙ​አ​ች​ኋል፤ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ችም ይወ​ስ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ያስ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ስለ ስሜም ወደ ነገ​ሥ​ታ​ትና ወደ መሳ​ፍ​ንት ይወ​ስ​ዱ​አ​ች​ኋል።


“ዓለም ቢጠ​ላ​ችሁ አስ​ቀ​ድሞ እኔን እንደ ጠላ ዕወቁ።


ነገር ግን ስለ ስሜ ይህን ሁሉ ያደ​ር​ጉ​ባ​ች​ኋል፤ የላ​ከ​ኝን አያ​ው​ቁ​ት​ምና።


ከም​ኵ​ራ​ባ​ቸው ያስ​ወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ ደግ​ሞም እና​ን​ተን የሚ​ገ​ድ​ላ​ችሁ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ያ​ቀ​ርብ የሚ​መ​ስ​ል​በት ጊዜ ይመ​ጣል።


ነገር ግን በዚህ ነገር በየ​ስ​ፍ​ራው ሁሉ እን​ዲ​ጣሉ በእኛ ዘንድ ታው​ቋ​ልና የአ​ን​ተን ዐሳብ ደግሞ ከአ​ንተ እን​ሰማ ዘንድ እን​ወ​ድ​ዳ​ለን።”


እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስም፥ “ጌታዬ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ነፍ​ሴን ተቀ​በል” እያለ ሲጸ​ልይ ይወ​ግ​ሩት ነበር።


ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።


ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፤ ዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።


“የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።


እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። አለኝም “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios