Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማቴዎስ 15:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ብዙ ሕዝብም አንካሶችን፥ ዕውሮችንም፥ ድዳዎችንም፥ ጉንድሾችንም፥ ሌሎችንም ብዙ ይዘው ወደ እርሱ ቀረቡ በኢየሱስም እግር አጠገብ አስቀመጡአቸው፤ ፈወሳቸውም፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ቍጥሩ ብዙ የሆነ ሕዝብም ዐንካሶችን፣ ዐይነ ስውሮችን፣ ሽባዎችን፣ ዲዳዎችን እንዲሁም ሌሎች ብዙዎችን ሕመምተኞች ይዘው ወደ እርሱ በማምጣት በእግሮቹ ሥር አስቀመጧቸው፤ እርሱም ፈወሳቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ብዙ ሕዝብም አንካሶችን፥ ዕውሮችን፥ ሽባዎችን፥ ዲዳዎችን፥ ሌሎችንም ብዙ ይዘው ወደ እርሱ መጡ፥ በኢየሱስም እግር ሥር አስቀመጡአቸው፤ እርሱም ፈወሳቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ብዙ ሰዎች አንካሶችን፥ ዕውሮችን፥ ሽባዎችን፥ ድዳዎችንና ሌሎችንም በሽተኞች ይዘው ወደ ኢየሱስ መጡ፤ በእግሩም ሥር አስቀመጡአቸው፤ እርሱም ፈወሳቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ብዙ ሕዝብም አንካሶችን፥ ዕውሮችንም፥ ዲዳዎችንም፥ ጉንድሾችንም፥ ሌሎችንም ብዙ ይዘው ወደ እርሱ ቀረቡ፥ በኢየሱስም እግር አጠገብ ጣሉአቸው፤ ፈወሳቸውም፤

Ver Capítulo Cópia de




ማቴዎስ 15:30
14 Referências Cruzadas  

እል​ፍ​ኙን በውኃ የሚ​ሠራ፥ ደመ​ናን መሄ​ጃው የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በነ​ፋስ ክን​ፍም የሚ​ሄድ፥


እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመሄድ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻላል።


ነገር ግን በበ​ዓል ምሳ በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ድሆ​ች​ንና ጦም አዳ​ሪ​ዎ​ችን፥ ዕው​ሮ​ችን፥ እጅና እግ​ርም የሌ​ላ​ቸ​ውን ጥራ።


“እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እን​ደ​ም​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ባደ​ረ​ገው በከ​ሃ​ሊ​ነቱ በተ​አ​ም​ራ​ቱና በድ​ንቅ ሥራ​ዎቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ለ​ጠ​ላ​ች​ሁን ሰው የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን ስሙ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios