Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማቴዎስ 13:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፤ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ፤ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 ዓሣ አጥማጆቹ መረቡ ሲሞላላቸው ጐትተው ወደ ባሕሩ ዳር አወጡት፤ ከዚያም ተቀምጠው ጥሩ ጥሩውን እየለዩ በቅርጫት ውስጥ ጨመሩ፤ መጥፎ መጥፎውን ግን ጣሉት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 በሞላች ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፤ ተቀምጠውም መልካሞቹን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አስቀመጡ፤ ክፉውን ግን ጣሉት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 በሞላች ጊዜ ዓሣ አጥማጆቹ ወደ ባሕሩ ዳር ጐትተው ያወጡአታል፤ ተቀምጠውም መልካም መልካሙን መርጠው በዕቃ ያስቀምጣሉ፤ መጥፎ መጥፎውን ግን ወዲያ ይጥላሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፥ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት።

Ver Capítulo Cópia de




ማቴዎስ 13:48
6 Referências Cruzadas  

ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን “እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ፤” እላለሁ’ አለ።”


“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዐይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤


በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኀጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፤ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤


መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios