Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማቴዎስ 13:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ‘መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፤ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እንዲህ ተብሎ የተነገረው የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል፤ “ ‘መስማትንስ ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እንዲህ ተብሎ የተነገረው የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል። መስማትን ትሰማላችሁ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ ነገር ግን አትመለከቱም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው በእነርሱ ላይ ይፈጸማል፦ ‘መስማትንስ ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አታደርጉም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም።

Ver Capítulo Cópia de




ማቴዎስ 13:14
11 Referências Cruzadas  

እና​ንተ ሰነ​ፎች ልበ ቢሶች፥ ዐይን እያ​ላ​ችሁ የማ​ታዩ፥ ጆሮም እያ​ላ​ችሁ የማ​ት​ሰሙ ሕዝብ ሆይ! ይህን ስሙ።


“የሰው ልጅ ሆይ! በዐ​መ​ፀኛ ቤት መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ሃል፤ እነ​ርሱ ያዩ ዘንድ ዐይን አላ​ቸው ነገር ግን አያ​ዩም፤ ይሰ​ሙም ዘንድ ጆሮ አላ​ቸው፤ ነገር ግን አይ​ሰ​ሙም፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ምሥ​ጢር ማወቅ ለእ​ና​ንተ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ለእ​ነ​ዚያ ግን አይ​ተው እን​ዳ​ያዩ፥ ሰም​ተ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም በም​ሳሌ ነው።


ነገር ግን ሁሉም የወ​ን​ጌ​ልን ትም​ህ​ርት የሰሙ አይ​ደ​ለም፤ ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “አቤቱ፥ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ን​ንስ ማን አመነ? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ክንዱ ለማን ተገ​ለጠ?” ብሎ​አ​ልና።


ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ልባ​ቸው ተሸ​ፍ​ኖ​አል፤ ያም መጋ​ረጃ ብሉይ ኪዳን በተ​ነ​በ​በት ዘመን ሁሉ ጸንቶ ኖሮ​አል፤ ክር​ስ​ቶስ እስ​ኪ​ያ​ሳ​ል​ፈው ድረስ አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ምና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ታስ​ተ​ውሉ ዘንድ ልብን፥ ታዩም ዘንድ ዐይ​ንን፥ ትሰ​ሙም ዘንድ ጆሮ​ዎ​ችን እስከ ዛሬ ድረስ አል​ሰ​ጣ​ች​ሁም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios