Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማቴዎስ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ማንም ሰው ሊያስተናግዳችሁ ወይም የምትናገሩትን ሊሰማ ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ከቤቱ ወይም ከከተማው ስትወጡ የእግሮቻችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ማንም የማይቀበላችሁ ወይም ቃላችሁን የማይሰማ ከሆነ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉችሁ ውጡ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ማንም ሰው የማይቀበላችሁ ወይም ቃላችሁን የማይሰማ ቢሆን ያንን ቤት ወይም ከተማ ለቃችሁ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ።

Ver Capítulo Cópia de




ማቴዎስ 10:14
14 Referências Cruzadas  

ደግ​ሞም ልብ​ሴን አራ​ገ​ፍ​ሁና፥ “ይህን ነገር የማ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሰው ከቤ​ቱና ከሥ​ራው እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያራ​ግ​ፈው፤ እን​ዲሁ የተ​ራ​ገ​ፈና ባዶ ይሁን” አልሁ። ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ፥ “አሜን” አሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ ሕዝ​ቡም እን​ደ​ዚህ ነገር አደ​ረጉ።


ቤቱም የሚገባው ቢሆን ሰላማችሁ ይድረስለት፤ ባይገባው ግን ሰላማችሁ ይመለስላችሁ።


“እንደዚህም ያለውን አንድ ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤


ከማይቀበሉአችሁና ከማይሰሙአችሁ ስፍራ ሁሉ፥ ከዚያ ወጥታችሁ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ ከእግራችሁ በታች ያለውን ትቢያ አራግፉ። እውነት እላችኋለሁ፤ ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ በፍርድ ቀን ይቀልላቸዋል፤” አላቸው።


“እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን እንጂ እኔን አይቀበልም አላቸው።”


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በስሜ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሕፃን የሚ​ቀ​በል እኔን ይቀ​በ​ላል፥ እኔ​ንም የሚ​ቀ​በል የላ​ከ​ኝን ይቀ​በ​ላል፤ ራሱን ከሁሉ ዝቅ የሚ​ያ​ደ​ርግ እርሱ ታላቅ ይሆ​ናል።”


የማ​ይ​ቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ቢሆን ግን ከዚ​ያች ከተማ ወጥ​ታ​ችሁ ምስ​ክር ሊሆ​ን​ባ​ቸው የእ​ግ​ራ​ች​ሁን ትቢያ አራ​ግፉ።”


እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ል​ከ​ውን የሚ​ቀ​በል እኔን ይቀ​በ​ላል፤ እኔ​ንም የሚ​ቀ​በል የላ​ከ​ኝን ይቀ​በ​ላል።”


እነ​ርሱ ግን የእ​ግ​ራ​ቸ​ውን ትቢያ አራ​ግ​ፈ​ው​ባ​ቸው ወደ ኢቆ​ን​ዮን ሄዱ።


እነ​ር​ሱም በተ​ቃ​ወ​ሙ​ትና በሰ​ደ​ቡት ጊዜ ልብ​ሱን አራ​ግፎ፥ “እን​ግ​ዲህ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ደማ​ችሁ በራ​ሳ​ችሁ ላይ ነው፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ ወደ አሕ​ዛብ እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው።


እንግዲህ የማይቀበል ሰውን ያልተቀበለ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስን በእናንተ እንዲኖር የሰጠውን እግዚአብሔርን ነው እንጂ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios