Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማርቆስ 11:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ደግሞም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። እርሱም በመቅደስ ሲመላለስ፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ሽማግሌዎችም ወደ እርሱ መጥተው

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እንደ ገና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚዘዋወርበት ጊዜ፣ የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና የሕዝብ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ ቀርበው፣

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚዘዋወርበት ጊዜ፥ የካህናት አለቆች፥ ጸሐፍትና የሕዝብ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ ቀርበው፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እንደገናም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ኢየሱስም በቤተ መቅደስ ውስጥ ሲዘዋወር ሳለ የካህናት አለቆች፥ የሕግ መምህራንና ሽማግሌዎች ወደ እርሱ መጡና

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ደግሞም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። እርሱም በመቅደስ ሲመላለስ፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ሽማግሌዎችም ወደ እርሱ መጥተው፦

Ver Capítulo Cópia de




ማርቆስ 11:27
10 Referências Cruzadas  

እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ? ወይስ እነዚህን ለማድረግ ይህን ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት።


ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ በሰ​ሎ​ሞን ደጅ መመ​ላ​ለሻ ይመ​ላ​ለስ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ ለዓ​ለም በግ​ልጥ ተና​ገ​ርሁ፤ አይ​ሁድ ሁሉ በሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት በም​ኵ​ራ​ብም፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ሁል​ጊዜ አስ​ተ​ማ​ርሁ፤ በስ​ው​ርም የተ​ና​ገ​ር​ሁት አን​ዳች ነገር የለም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios