Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እኔም እኮ ገዢ ሰው ነኝ፤ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሉኝ፤ አን​ዱን ሂድ ብለው ይሄ​ዳል፤ ሌላ​ው​ንም ና ብለው ይመ​ጣል፤ አገ​ል​ጋ​ዬ​ንም እን​ዲህ አድ​ርግ ብለው ያደ​ር​ጋል።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እኔ ራሴ የበላይ አለቃ አለኝ፤ ከበታቼም የማዝዛቸው ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን፣ ‘ሂድ’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን፣ ‘ና’ ስለው ይመጣል፤ ባሪያዬንም፣ ‘ይህን አድርግ’ ስለው ያደርጋል።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እኔ በእርግጥ ከሌሎች ሥልጣናት በታች የተሾምሁ ሰው ነኝ፤ ከእኔም በታች ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱንም ‘ሂድ!’ ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና!’ ብለው ይመጣል፤ ኣገልጋዬንም ‘ይህን አድርግ!’ ብለው ያደርጋል።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እኔ ራሴ ለባለ ሥልጣኖች ታዛዥ ስሆን ከእኔ በታች የማዛቸው ወታደሮች አሉኝ። ስለዚህ አንዱን ‘ሂድ!’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን ‘ና!’ ስለው ይመጣል፤ አገልጋዬንም ‘ይህን አድርግ!’ ስለው ያደርጋል።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እኔ ደግሞ ከሌሎች በታች የምገዛ ሰው ነኝ፥ ከእኔም በታች ወታደሮች አሉኝ፥ አንዱንም፦ ሂድ ብለው ይሄዳል፥ ሌላውንም፦ ና ብለው ይመጣል፥ ባሪያዬንም፦ ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 7:8
12 Referências Cruzadas  

እኔም ወደ አንተ ልመጣ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን በቃ​ልህ እዘዝ፤ ብላ​ቴ​ና​ዬም ይድ​ናል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ከእ​ርሱ በሰማ ጊዜ አደ​ነ​ቀው፤ ዘወር ብሎም ይከ​ተ​ሉት ለነ​በ​ሩት ሕዝብ፥ “እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልስ እንኳ እን​ዲህ ያለ እም​ነት ያለው ሰው አላ​ገ​ኘ​ሁም” አላ​ቸው።


ጳው​ሎ​ስም ከመቶ አለ​ቆች አን​ዱን ጠርቶ፥ “የሚ​ነ​ግ​ረው ነገር አለና ይህን ልጅ ወደ የሻ​ለ​ቃው አድ​ር​ስ​ልኝ” አለው።


ከመቶ አለ​ቆ​ችም ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “ከወ​ታ​ደ​ሮች ሁለት መቶ ሰውና ሰባ ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሁለት መቶ ቀስ​ተ​ኞ​ችም ምረጡ፤ ከሌ​ሊ​ቱም በሦ​ስት ሰዓት ወደ ቂሣ​ርያ ይሂዱ” አላ​ቸው።


“ከሉ​ስ​ዮስ ቀላ​ው​ዴ​ዎስ፥ ለክ​ቡር አገረ ገዢ ፊል​ክስ፥ ሰላም ለአ​ንተ ይሁን።


ጭፍ​ሮ​ችም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም በሌ​ሊት ወሰ​ዱት፤ ወደ አን​ቲ​ጳ​ጥ​ሪ​ስም አደ​ረ​ሱት።


የመቶ አለ​ቃ​ው​ንም ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ጠ​ብ​ቀው፥ በሰፊ ቦታም እን​ዲ​ያ​ኖ​ረው፥ እን​ዳ​ያ​ጠ​ብ​በ​ትም፥ ሊያ​ገ​ለ​ግ​ሉት በመጡ ጊዜም ከወ​ዳ​ጆቹ አን​ዱን ስንኳ እን​ዳ​ይ​ከ​ለ​ክ​ል​በት አዘዘ።


ነገር ግን ስለ እርሱ ወደ ጌታዬ የም​ጽ​ፈው የታ​ወቀ ነገር የለ​ኝም። ስለ​ዚህ ከተ​መ​ረ​መረ በኋላ የም​ጽ​ፈ​ውን አገኝ ዘንድ ወደ እና​ንተ ይል​ቁ​ንም ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ ወደ አንተ አመ​ጣ​ሁት።


አገ​ል​ጋ​ዮች ሆይ በቅን ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት እንጂ ለሰው ደስ እን​ደ​ም​ታ​ሰኙ ለታ​ይታ የም​ት​ገዙ ሳት​ሆኑ፥ በሥጋ ጌቶ​ቻ​ችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios