Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 6:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 ቃሌን ሰምቶ የማ​ያ​ደ​ር​ገው ሰው ግን ቤቱን ያለ መሠ​ረት በአ​ፈር ላይ የሠራ ሰውን ይመ​ስ​ላል፤ ጎር​ፎች ገፉት፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ወደቀ፤ የዚ​ያም ቤት አወ​ዳ​ደቁ ታላቅ ሆነ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ግን ቤቱን ያለ መሠረት በዐፈር ላይ የሠራን ሰው ይመስላል፤ የወንዝ ሙላትም ቤቱን በመታው ጊዜ ወዲያው ወደቀ፤ ክፉኛም ፈራረሰ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 ነገር ግን ሰምቶ የማያደርገው ቤቱን ያለ መሠረት በምድር ላይ የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ወንዙም ገፋው፤ ወዲያውም ወደቀ የዚያ ቤት አወዳደቅም ታላቅ ሆነ።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ግን ያለ መሠረት ቤቱን በዐፈር ላይ የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ጐርፍ መጥቶ ያንን ቤት በገፋው ጊዜ ወዲያውኑ ወደቀ፤ አወዳደቁም እጅግ ታላቅ ሆነ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

49 ሰምቶ የማያደርገው ግን ያለ መሠረት በምድር ላይ ቤቱን የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ወንዙም ገፋው ወዲያውም ወደቀ የዚያ ቤት አወዳደቅም ታላቅ ሆነ።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 6:49
30 Referências Cruzadas  

ሕዝብ እን​ደ​ሚ​መጣ ወደ አንተ ይመ​ጣሉ፤ እንደ ሕዝ​ቤም በፊ​ትህ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ፤ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም፤ በአ​ፋ​ቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባ​ቸ​ውም ጣዖ​ታ​ትን ይከ​ተ​ላ​ልና።


ወን​ዶ​ችም ደግሞ ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ይጫ​ወ​ታ​ሉና፥ ከጋ​ለ​ሞ​ቶ​ችም ጋር ይሠ​ዋ​ሉና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ በሰ​ሰኑ ጊዜ፥ ሙሽ​ሮ​ቻ​ች​ሁም በአ​መ​ነ​ዘሩ ጊዜ አል​ቀ​ጣ​ኋ​ቸ​ውም፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ው​ልም ሕዝብ ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር ይቀ​ላ​ቀ​ላል።


ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ።


በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤


ለጊዜው ነው እንጂ በእነርሱ ሥር የላቸውም፤ ኋላም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላሉ።


የጌ​ታ​ውን ፈቃድ ዐውቆ እንደ ፈቃዱ የማ​ይ​ሠ​ራና የማ​ያ​ዘ​ጋጅ የዚያ አገ​ል​ጋይ ቅጣቱ ብዙ ነው።


የሀ​ገሩ ሰዎች ግን ይጠ​ሉት ነበ​ርና፥ ይህ በእኛ ላይ ሊነ​ግሥ አን​ሻም ብለው አከ​ታ​ት​ለው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ።


ነገር ግን እነ​ዚ​ያን ልነ​ግ​ሥ​ባ​ቸው ያል​ወ​ደ​ዱ​ትን ጠላ​ቶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጡና በፊቴ ውጉ​አ​ቸው።”


“ለምን አቤቱ፥ አቤቱ፥ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ? የም​ላ​ች​ሁ​ንም አታ​ደ​ር​ጉም።


መሠ​ረ​ቱን አጥ​ልቆ ቈፍሮ የመ​ሠ​ረ​ተና ቤቱን በዐ​ለት ላይ የሠራ ሰውን ይመ​ስ​ላል፤ ብዙ ፈሳ​ሾች በመጡ ጊዜ ጎር​ፎች ያን ቤት ገፉት፤ ሊያ​ነ​ዋ​ው​ጡ​ትም አል​ቻ​ሉም፤ በዐ​ለት ተሠ​ር​ቶ​አ​ልና።


ለሕ​ዝ​ቡም ቃሉን ነግሮ ከፈ​ጸመ በኋላ ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ገባ።


በእኔ ያለ​ውን፥ ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫ​ፍም ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ደ​ዋል፤ የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን ቅር​ን​ጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እን​ዲ​ያ​ፈራ ያጠ​ራ​ዋል።


ከእኔ በኋላ ለመ​ን​ጋ​ዪቱ የማ​ይ​ራሩ ነጣ​ቂ​ዎች ተኵ​ላ​ዎች እን​ደ​ሚ​መጡ እኔ አው​ቃ​ለሁ።


በየ​ም​ኵ​ራቡ ሁሉ የማ​ስ​ገ​ደጃ ማዘዣ አም​ጥቼ፥ በግድ የኢ​የ​ሱ​ስን ስም እን​ዲ​ሰ​ድቡ ዘወ​ትር መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው ነበር፤ ይል​ቁ​ንም ወደ ሌሎች ከተ​ማ​ዎች እያ​ሳ​ደ​ድሁ ከፋ​ሁ​ባ​ቸው።


ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ “ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል፤ ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፤” ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።


በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዕውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል።


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios