Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 4:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ወደ ገሊላ ከተ​ማም ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ወረደ፤ በሰ​ን​በ​ትም ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከዚያም በገሊላ አውራጃ ወደምትገኘው ከተማ ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም በሰንበት ዕለት ሕዝቡን ያስተምር ጀመር፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 የገሊላ ከተማም ወደ ሆነችው ወደ ቅፍርናሆም ወረደ። በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ከዚህም በኋላ፥ ኢየሱስ በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ከተማ ወደ ቅፍርናሆም ሄደ፤ በዚያም፥ ሕዝቡን በሰንበት ቀን ያስተምር ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ወደ ገሊላ ከተማም ወደ ቅፍርናሆም ወረደ። በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር፤

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 4:31
14 Referências Cruzadas  

በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።


ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።


እር​ሱም፥ “በውኑ ባለ መድ​ኀ​ኒት ራስ​ህን አድን፤ በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ያደ​ረ​ግ​ኸ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ሁሉ በዚ​ህም በሀ​ገ​ርህ ደግሞ አድ​ርግ ብላ​ችሁ ይህ​ችን ምሳሌ ትመ​ስ​ሉ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።


አይ​ሁድ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ የከ​በሩ ሴቶ​ች​ንና የከ​ተ​ማ​ውን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች አነ​ሳ​ሡ​አ​ቸው፤ በጳ​ው​ሎ​ስና በበ​ር​ና​ባስ ላይም ስደ​ትን አስ​ነሡ፤ ከሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው።


ጳው​ሎ​ስም በየ​ሰ​ን​በቱ በም​ኵ​ራብ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ አይ​ሁ​ድ​ንና አረ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ያሳ​ም​ና​ቸው ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios