Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 22:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ነገር ግን፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ እን​ግ​ዲህ ከእ​ርሱ እን​ደ​ማ​ል​በላ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት የዚህ ትርጕም እስኪፈጸም ድረስ ይህን ፋሲካ ዳግመኛ አልበላም።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም እላችኋለሁና፤” አላቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የዚህ ነገር እውነተኛ ምሥጢር በእግዚአብሔር መንግሥት ፍጹም ሆኖ እስኪገለጥ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ ይህን የፋሲካ ራት ከቶ አልበላም እላችኋለሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እላችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም አላቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 22:16
11 Referências Cruzadas  

ጌታ​ቸው በመጣ ጊዜ እን​ዲህ ሲያ​ደ​ር​ጉና ሲተጉ የሚ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አገ​ል​ጋ​ዮች ብፁ​ዓን ናቸው፤ እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወገ​ቡን ታጥቆ በማ​ዕድ ያስ​ቀ​ም​ጣ​ቸ​ዋል፤ እየ​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም ያገ​ለ​ግ​ላ​ቸ​ዋል።


ለምሳ ከተ​ቀ​መ​ጡ​ትም አንዱ ይህን ሰምቶ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እህል የሚ​በላ ብፁዕ ነው” አለው።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከመ​ከ​ራዬ አስ​ቀ​ድሞ ይህን ፋሲካ ከእ​ና​ንተ ጋር ልበላ እጅግ ወደ​ድሁ።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እስ​ክ​ት​መጣ ድረስ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከዚህ የወ​ይን ፍሬ አል​ጠ​ጣም።”


በመ​ን​ግ​ሥቴ በማ​ዕዴ ትበ​ሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በወ​ን​በ​ሮ​ችም ተቀ​ም​ጣ​ችሁ በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ትፈ​ርዱ ዘንድ።”


የሰው ልጅ ለሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ለሚ​ኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚ​ጠ​ፋው መብል አይ​ደ​ለም፤ ይህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ አት​ሞ​ታ​ልና።”


ይኸ​ውም ለሕ​ዝቡ ሁሉ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን አስ​ቀ​ድሞ ለመ​ረ​ጣ​ቸ​ውና ምስ​ክ​ሮች ለሚ​ሆ​ኑት ብቻ ነው እንጂ፤ የመ​ረ​ጣ​ቸው የተ​ባ​ል​ንም እኛ ነን፤ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ ከተ​ነሣ በኋላ ከእ​ርሱ ጋር የበ​ላን የጠ​ጣ​ንም እኛ ነን።


መልአኩም “ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው፤” ብለህ ጻፍ፤ አለኝ። ደግሞም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው፤” አለኝ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios