Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 20:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አም​ጥ​ተ​ውም አሳ​ዩት፤ “መልኩ፥ ጽሕ​ፈ​ቱስ የማ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የቄ​ሣር ነው” ብለው መለ​ሱ​ለት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “እስኪ አንድ ዲናር አሳዩኝ፤ በላዩ ያለው የማን መልክና ጽሕፈት ነው?” እነርሱም፣ “የቄሳር ነው” ብለው መለሱለት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “አንድ ዲናር አሳዩኝ፤ መልኩና ጽሑፉ የማን ነው?” አላቸው። ሲመልሱም “የቄሣር ነው” አሉት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “እስቲ ገንዘቡን አሳዩኝ፤ በዚህ ገንዘብ ላይ የተቀረጸው መልክና የተጻፈው ስም የማን ነው?” እነርሱም “የሮም ንጉሠ ነገሥት ነው” አሉት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 መልኩ ጽሕፈቱስ የማን ነው? አላቸው። መልሰውም፦ የቄሣር ነው አሉት።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 20:24
14 Referências Cruzadas  

ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና ‘ዕዳህን ክፈለኝ’ ብሎ ያዘና አነቀው።


ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው።


እርሱም “ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት?” አላቸው።


እነርሱም አመጡለት። “ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት?” አላቸው፤ እነርሱም “የቄሳር ናት፤” አሉት።


በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ፤ ሰው ሁሉ ይቈ​ጠር ዘንድ ከአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ቄሣር ትእ​ዛዝ ወጣ።


ለቄ​ሣር ግብር መስ​ጠት ይገ​ባል? ወይስ አይ​ገ​ባም?”


ተን​ኰ​ላ​ቸ​ው​ንም ዐውቆ፥ “ለምን ትፈ​ት​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ? ገን​ዘ​ቡን አሳ​ዩኝ” አላ​ቸው።


እር​ሱም፥ “እን​ኪ​ያስ የቄ​ሣ​ርን ለቄ​ሣር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጡ” አላ​ቸው።


እን​ዲ​ህም እያሉ ይከ​ስ​ሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄ​ሣር ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሲከ​ለ​ክ​ልና ሕዝ​ቡን ሲያ​ሳ​ምፅ፥ ራሱ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ክር​ስ​ቶ​ስን ሲያ​ደ​ርግ አገ​ኘ​ነው።”


ጢባ​ር​ዮስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አም​ስት ዓመት ጴን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ የይ​ሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮ​ድ​ስም በገ​ሊላ የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወን​ድሙ ፊል​ጶ​ስም የኢ​ጡ​ር​ያ​ስና የጥ​ራ​ኮ​ኒ​ዶስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳ​ን​ዮ​ስም የሳ​ብ​ላ​ኒስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥


ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አጋ​ቦስ የተ​ባለ አንድ ሰው ተነ​ሥቶ በዓ​ለም ሁሉ ጽኑ ረኃብ እን​ደ​ሚ​መጣ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ተገ​ል​ጦ​ለት ተና​ገረ፤ ይህም በቄ​ሣር ቀላ​ው​ዴ​ዎስ ዘመን ሆነ።


አግ​ሪ​ጳም ፊስ​ጦ​ስን፥ “ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ባይል ኖሮ ይህ ሰው ይፈታ ዘንድ በተ​ገባ ነበር” አለው።


ቅዱ​ሳ​ንም ሁሉ፥ ይል​ቁ​ንም ከቄ​ሣር ቤተ ሰብእ የሆኑ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios