Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 18:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ዐሥራ ሁለ​ቱ​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ወ​ጣ​ለን፤ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈው ሁሉ በሰው ልጅ ላይ ይፈ​ጸ​ማል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻ ወስዶ እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ ነቢያት ስለ ሰው ልጅ የጻፉትም ሁሉ ይፈጸማል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ዐሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው “እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ ስለ ሰው ልጅም በነቢያት የተጻፈው ሁሉ ይፈጸማል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ! ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ ስለ ሰው ልጅ በነቢያት የተጻፈው ሁሉ በዚያ ይፈጸማል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 አሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ ስለ ሰው ልጅም በነቢያት የተጻፈው ሁሉ ይፈጸማል።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 18:31
17 Referências Cruzadas  

ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።


ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።


“ጌታ ሆይ! ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ፤’ እንዳለ ትዝ አለን።


የበሉትም አራት ሺህ ያህል ነበሩ፤ አሰናበታቸውም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አንድ ሰው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ኢያ​ሪኮ ይወ​ርድ ነበር፤ ሽፍ​ቶ​ችም አገ​ኙት፤ ደበ​ደ​ቡት፥ አቈ​ሰ​ሉት፥ ልብ​ሱ​ንም ገፍ​ፈው፤ በሕ​ይ​ወ​ትና በሞት መካ​ከል ጥለ​ውት ሄዱ።


“ለሰው ልጅ ብዙ መከራ ያጸ​ኑ​በት ዘንድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችም ይፈ​ት​ኑት ዘንድ፥ ይገ​ድ​ሉ​ትም ዘንድ፥ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነሣ ዘንድ አለው” አላ​ቸው።


የመ​ው​ጣቱ ወራ​ትም በቀ​ረበ ጊዜ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሄድ ፊቱን አቀና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios