Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “አራሽ ወይም ከብት ጠባቂ አገ​ል​ጋይ ያለው ከእ​ና​ንተ ማን ነው? ከእ​ር​ሻው በተ​መ​ለሰ ጊዜ ጌታው ና፥ ፈጥ​ነህ ወደ​ዚህ ውጣና ከእኔ ጋር በማ​ዕድ ተቀ​መጥ ይለ​ዋ​ልን?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ከእናንተ መካከል አንድ ሰው ዐራሽ ወይም በግ ጠባቂ የሆነ ባሪያ ቢኖረው፣ ከዕርሻ የተመለሰውን ባሪያውን፣ ‘ቶሎ ወደ ማእድ ቅረብ’ ይለዋልን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ አገልጋይ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ ‘ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ፤’ የሚለው ማን ነው?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ከእናንተ አንዱ በእርሻ ሥራ የተሰማራ፥ ወይም በጎች የሚጠብቅ አገልጋይ ቢኖረው፥ አገልጋዩ ከሥራው በተመለሰ ጊዜ ወዲያውኑ ‘ና ተቀመጥና ራትህን ብላ’ ይለዋልን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ ባሪያ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ፦ ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ የሚለው ማን ነው?

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 17:7
6 Referências Cruzadas  

እርሱ ግን “ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው?


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አላ​ቸው፥ “እና​ንት ግብ​ዞች፥ እና​ን​ተሳ አህ​ያ​ች​ሁን ወይም በሬ​አ​ች​ሁን በሰ​ን​በት ቀን ገለባ ከሚ​በ​ላ​በት አት​ፈ​ቱ​ት​ምን? ውኃ ልታ​ጠ​ጡ​ትስ አት​ወ​ስ​ዱ​ት​ምን?


“ከእ​ና​ንተ በሬው ወይም አህ​ያው በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ የወ​ደ​ቀ​በት አንድ ሰው ቢኖር ዕለ​ቱን በሰ​ን​በት ቀን ያነ​ሣው የለ​ምን?” አላ​ቸው።


በኖኅ ዘመን እንደ ሆነው የሰው ልጅ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ እን​ዲሁ ይሆ​ናል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሰ​ና​ፍጭ ቅን​ጣት ታህል እም​ነት ብት​ኖ​ራ​ችሁ ይህ​ችን ሾላ ከሥ​ርሽ ተነ​ቅ​ለሽ በባ​ሕር ውስጥ ተተ​ከዪ ብት​ሉ​አት ትታ​ዘ​ዝ​ላ​ች​ኋ​ለች።”


እራ​ቴን አዘ​ጋ​ጅ​ልኝ፥ እስ​ክ​በ​ላና እስ​ክ​ጠጣ ድረ​ስም ታጥ​ቀህ አሳ​ል​ፍ​ልኝ፤ ከዚ​ህም በኋላ አንተ ብላ፥ ጠጣም ይለው የለ​ምን?


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios