Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 15:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ፥ ወዳ​ጆ​ቹ​ንና ጎረ​ቤ​ቶ​ቹን ጠርቶ፦ የጠ​ፋ​ች​ኝን በጌን አግ​ኝ​ቼ​አ​ታ​ለ​ሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ ይላ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹንም በአንድነት ጠርቶ፣ ‘የጠፋውን በጌን አግኝቻለሁና ከእኔ ጋራ ደስ ይበላችሁ’ ይላቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ ‘የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ፤’ ይላቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ወደ ቤቱም በደረሰ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ ‘የጠፋውን በጌን አግኝቼአለሁና ደስ ብሎኛል ደስ ይበላችሁ!’ ይላቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፦ የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 15:6
19 Referências Cruzadas  

ዘመ​ዶ​ች​ዋና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ቱን እን​ዳ​በ​ዛ​ላት በሰሙ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ደስ አላ​ቸው።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ እን​ዲሁ ንስሓ ስለ​ሚ​ገባ ስለ አንድ ኀጢ​ኣ​ተኛ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት በሰ​ማ​ያት ደስታ ይሆ​ናል።”


ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ነበር፤ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና ደስ ይላ​ቸ​ውም ጀመር።


በአ​ገ​ኛ​ትም ጊዜ ደስ ብሎት በት​ከ​ሻው ላይ ይሸ​ከ​ማ​ታል።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ እን​ዲሁ ንስሓ ከማ​ያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸው ከዘ​ጠና ዘጠኙ ጻድ​ቃን ይልቅ ንስሓ ስለ​ሚ​ገባ ስለ አንድ ኀጢ​ኣ​ተኛ በሰ​ማ​ያት ፍጹም ደስታ ይሆ​ናል።


እና​ን​ተስ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ ካደ​ረ​ጋ​ችሁ ወዳ​ጆች ናችሁ።


ሙሽራ ያለ​ችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚ​ሰ​ማው የሙ​ሽ​ራው ሚዜ ግን በሙ​ሽ​ራው ቃል እጅግ ደስ ይለ​ዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈ​ጸ​መች።


በደ​ረሰ ጊዜም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸን​ተው ይኖሩ ዘንድ መከ​ራ​ቸው።


ከቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም በተ​ላኩ ጊዜ ወደ ሰማ​ር​ያና ወደ ፊንቄ ደር​ሰው አሕ​ዛብ ወደ ሃይ​ማ​ኖት እንደ ተመ​ለሱ ነገ​ሩ​ቸ​አ​ቸው፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰ​ኙ​አ​ቸው።


ስለ እና​ን​ተም ሁል​ጊዜ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ የደ​ስታ ጸሎ​ትም አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ሁም የአ​ም​ልኮ መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ። እነ​ሆም እኔ በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የም​ና​ፍ​ቃ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ደስ​ታ​ች​ንና አክ​ሊ​ላ​ችን ናችሁ፤ ወዳ​ጆ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ዲህ ቁሙ፤ በጌ​ታ​ች​ንም ጽኑ።


ተስፋችን ወይስ ደስታችን ወይስ የትምክህታችን አክሊል ማን ነው? በጌታችን በኢየሱስ ፊት በመምጣቱ እናንተ አይደላችሁምን?


እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።


እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios