Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ይህስ ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችን ይቀ​በ​ላል፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ይበ​ላል” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ፈሪሳውያንና ጸሐፍትም፣ “ይህ ሰው ኀጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋራ ይበላል” እያሉ አጕረመረሙ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ፈሪሳውያንና ጻፎችም “ይህስ ኀጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋር ይበላል፤” ብለው እርስ በርሳቸው አጉረመረሙ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ግን ይህን አይተው፦ “ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋር አብሮ ይበላል” እያሉ በኢየሱስ ላይ አጒረመረሙ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ፈሪሳውያንና ጻፎችም፦ ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 15:2
12 Referências Cruzadas  

የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘እነሆ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።”


ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል?” አሉአቸው።


እን​ዲ​ህም ብሎ መሰ​ለ​ላ​ቸው።


ሁሉም አይ​ተው “ወደ ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው ቤት ሊውል ገባ” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ከቀ​ራ​ጮ​ችና ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ለምን ትበ​ላ​ላ​ችሁ? ትጠ​ጡ​ማ​ላ​ችሁ?” ብለው በደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


የሰው ልጅም እየ​በ​ላና እየ​ጠጣ መጣ፤ እና​ንተ ግን እነሆ፥ በላ​ተ​ኛና ወይን ጠጪ ሰው፥ የኃ​ጥ​ኣ​ንና የቀ​ራ​ጮች ወዳጅ አላ​ች​ሁት።


የጠ​ራው ፈሪ​ሳ​ዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የም​ት​ዳ​ስ​ሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እን​ዴ​ትስ እንደ ነበ​ረች ባላ​ወ​ቀም ነበ​ርን? ኀጢ​አ​ተኛ ናትና።”


“ወደ አል​ተ​ገ​ረ​ዙት ሰዎች ቤት ገብ​ተህ አብ​ረ​ሃ​ቸው በል​ተ​ሃል” አሉት።


ሰዎች ከያ​ዕ​ቆብ ዘንድ ከመ​ም​ጣ​ታ​ቸው በፊት፥ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ጋር ይበላ ነበ​ርና፥ በመጡ ጊዜ ግን ተለ​ያ​ቸው፤ ከአ​ይ​ሁድ ወገን የሆ​ኑ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና።


“ኀጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ፤” የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios