Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 15:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በል​ቡም እን​ዲህ ብሎ ዐሰበ፦ እህል የሚ​ተ​ር​ፋ​ቸው የአ​ባቴ ሠራ​ተ​ኞች ምን ያህል ናቸው? እኔ ግን በዚህ በረ​ኃብ ልሞት ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ልብ በገዛ ጊዜ ግን እንዲህ አለ፤ ‘ስንቱ የአባቴ ሠራተኛ ምግብ ተርፎታል፤ እኔ ግን እዚህ በራብ ልሞት ተቃርቤአለሁ

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ ‘ምግብ የሚተርፋቸው የአባቴ ተቀጣሪዎች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በዚህ ጊዜ ልጁ ስሕተቱን ተገንዝቦ እንዲህ ሲል አሰበ፤ ‘በአባቴ ቤት ተቀጥረው የሚሠሩ አገልጋዮች እንጀራ እስኪጠግቡ በልተው የሚተርፋቸው ስንት ናቸው! እኔ ግን እዚህ በረሀብ መሞቴ ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 15:17
19 Referências Cruzadas  

ወደ ኪዳ​ን​ህም ተመ​ል​ከት፥ የም​ድር የጨ​ለማ ስፍ​ራ​ዎች በኃ​ጥ​ኣን ቤቶች ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።


ከፀ​ሓይ በታች የተ​ደ​ረ​ገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግ​ሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋ​ትን ትሞ​ላ​ለች፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ሳሉ ሁከት በል​ባ​ቸው አለ፥ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሙታን ይወ​ር​ዳሉ።


ከተ​መ​ለ​ስሁ በኋላ ተጸ​ጸ​ትሁ፤ ከተ​ገ​ሠ​ጽ​ሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፤ የብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ቴ​ንም ስድብ ተሸ​ክ​ሜ​አ​ለ​ሁና አፈ​ርሁ፥ ተዋ​ረ​ድ​ሁም።


ዛይ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀድሞ ወድዳ በሠ​ራ​ችው ሥራ ሁሉ የመ​ከ​ራ​ዋን ወራት አሰ​በች፤ ሕዝ​ብዋ በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች እጅ በወ​ደቀ ጊዜ፥ የሚ​ረ​ዳ​ትም በሌ​ላት ጊዜ፥ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች አዩ​አት፤ በመ​ፍ​ረ​ስ​ዋም ሳቁ።


ከሠ​ራው ሁሉ በደል አይቶ ተመ​ል​ሶ​አ​ልና ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።


ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም ትከ​ተ​ላ​ለች፤ ነገር ግን አት​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ውም፤ ትፈ​ል​ጋ​ቸ​ው​ማ​ለች፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኛ​ቸ​ውም፤ እር​ስ​ዋም፥ “ከዛሬ ይልቅ የዚ​ያን ጊዜ ይሻ​ለኝ ነበ​ርና ተመ​ልሼ ወደ ቀደ​መው ባሌ እሄ​ዳ​ለሁ” ትላ​ለች።


እሪ​ያ​ዎች ከሚ​መ​ገ​ቡት ተረ​ን​ቃ​ሞም ይጠ​ግብ ዘንድ ተመኘ፤ ግን የሚ​ሰ​ጠው አል​ነ​በ​ረም።


በሲ​ኦ​ልም በሥ​ቃይ ሳለ ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ አብ​ር​ሃ​ምን ከሩቅ አየው፤ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​ምጦ አየው።


ሰዎ​ችም የሆ​ነ​ውን ያዩ ዘንድ ወጡ፤ ሄደ​ውም ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ በደ​ረሱ ጊዜ አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ለ​ትን ያን ሰው አእ​ም​ሮዉ ተመ​ል​ሶ​ለት ልብ​ሱን ለብሶ፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር አጠ​ገብ ተቀ​ምጦ አገ​ኙ​ትና ፈሩ።


ያን​ጊ​ዜም የጴ​ጥ​ሮስ ልቡና ተመ​ለ​ሰ​ለ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ልኮ ከሄ​ሮ​ድስ እጅና የአ​ይ​ሁድ ሕዝብ ይጠ​ብ​ቁት ከነ​በ​ረው ሁሉ እንደ አዳ​ነኝ በእ​ው​ነት አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ።


ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ልባ​ቸው ተከ​ፈተ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ወን​ድ​ሞቹ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ምን እና​ድ​ርግ?” አሏ​ቸው።


“የተ​ኛህ ንቃ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይ​ተህ ተነሥ፤ ክር​ስ​ቶ​ስም ያበ​ራ​ል​ሃል” ብሎ​አ​ልና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios