Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 10:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አንድ ሰው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ኢያ​ሪኮ ይወ​ርድ ነበር፤ ሽፍ​ቶ​ችም አገ​ኙት፤ ደበ​ደ​ቡት፥ አቈ​ሰ​ሉት፥ ልብ​ሱ​ንም ገፍ​ፈው፤ በሕ​ይ​ወ​ትና በሞት መካ​ከል ጥለ​ውት ሄዱ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠው፤ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በወንበዴዎች እጅ ወደቀ፤ ልብሱንም ገፍፈው ደበደቡት፤ በሞት አፋፍ ላይ ጥለውት ሄዱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ፤ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት፤ ደበደቡትም፤ በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በመንገድ ላይ ሳለ ቀማኞች አግኝተውት ልብሱን ገፈፉት፤ ከደበደቡትም በኋላ ሊሞት ሲያጣጥር ጥለውት ሄዱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 10:30
7 Referências Cruzadas  

ዘር​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ፥ ዙፋ​ን​ህ​ንም ለልጅ ልጅ አጸ​ና​ለሁ።


ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ች​ዋን የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ር​ዋም ሁሉ የተ​ገ​ደ​ሉት ይወ​ድ​ቃሉ።


ላሜድ። በከ​ተማ ጎዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በእ​ና​ቶ​ቻ​ቸው ብብት እለይ-እለይ ባለች ጊዜ፥ እና​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ “እህ​ልና ወይን ወዴት አለ?” ይሉ​አ​ቸ​ዋል።


የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ንጉሥ ክንድ አበ​ረ​ታ​ለሁ፤ ሰይ​ፌ​ንም በእጁ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ግብ​ፅ​ንም ይወ​ጋ​በ​ታል፥ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ሰለ​ባ​ዋ​ንም ይሰ​ል​ባል።


አንድ ካህ​ንም በዚ​ያች መን​ገድ ሲወ​ርድ ድን​ገት አገ​ኘው፤ አይ​ቶም አል​ፎት ሄደ።


ዐሥራ ሁለ​ቱ​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ወ​ጣ​ለን፤ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈው ሁሉ በሰው ልጅ ላይ ይፈ​ጸ​ማል።


ይህ​ንም ተና​ግሮ ወደ ፊት ሄደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወጣ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios