Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከዚ​ህም በኋላ የሕ​ዝ​ቡን ቍር​ባን አቀ​ረበ፤ ስለ ሕዝቡ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሆ​ነ​ውን ፍየል ወስዶ አረ​ደው፤ አነ​ጻ​ውም፤ እንደ ፊተ​ኛ​ውም ለየው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አሮንም የሕዝቡን መሥዋዕት አቀረበ፤ ስለ ሕዝቡ የኀጢአት መሥዋዕት የሆነውን ፍየል ወስዶ ዐረደው፤ እንደ ፊተኛው ሁሉ ይህንም በኀጢአት መሥዋዕትነት ሠዋው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከዚያም በኋላ የሕዝቡን ቁርባን አቀረበ፤ ስለ ሕዝቡ ለኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን ፍየል ወስዶ አረደው፥ ስለ ኃጢአትም እንደ ፊተኛው የኃጢአት መሥዋዕት ሠዋው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚያም በኋላ ካህኑ የሕዝቡን መባ አቀረበ፤ ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን ተባዕት ፍየል ወስዶ ዐረደው፤ እርሱንም ስለ ራሱ ኃጢአት ባቀረበው ዐይነት መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የሕዝቡንም ቍርባን አቀረበ፤ ስለ ሕዝቡ ለኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን ፍየል ወስዶ አረደው፥ ስለ ኃጢአትም እንደ ፊተኛው ሠዋው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 9:15
11 Referências Cruzadas  

ካህ​ና​ቱም አረ​ዱ​አ​ቸው፤ ንጉ​ሡም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ እን​ዲ​ደ​ረግ አዝዞ ነበ​ርና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ርጉ ዘንድ ደማ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አቀ​ረቡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።


ሙሴም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል እጅግ ፈለ​ገው፤ በፈ​ለ​ገ​ውም ጊዜ እነሆ ተቃ​ጥሎ ነበር፤ ሙሴም የቀ​ሩ​ትን የአ​ሮ​ንን ልጆች አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን ተቈ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፦


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹ​ንም በውኃ አጠበ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ላይ ጨመ​ረው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች፦ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አውራ ፍየ​ልን፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ዓመት የሆ​ና​ቸ​ውን ጥጃና ጠቦ​ትን፥


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ስለ​ዚ​ህም የሕ​ዝ​ብን ኀጢ​አት ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ የሚ​ም​ርና የታ​መነ ሊቀ ካህ​ናት እን​ዲ​ሆን በነ​ገር ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሊመ​ስል ተገ​ባው።


በዚ​ህም ምክ​ን​ያት ስለ ሕዝብ እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ እን​ዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ስለ ኀጢ​አት ማቅ​ረብ ይገ​ባ​ዋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios