Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 6:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታ​ረ​ዳል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “አሮንንና ልጆቹን እንዲህ በላቸው፤ ‘ስለ ኀጢአት መሥዋዕት አቀራረብ የምትከተለው ሥርዐት ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኀጢአቱም መሥዋዕት እዚያው በእግዚአብሔር ፊት ይታረድ፤ ይህም እጅግ ቅዱስ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ ተናገር፦ የኃጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአቱ መሥዋዕት በጌታ ፊት ይታረዳል፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የኃጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርበው እንስሳ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ በእግዚአብሔር ፊት ይታረድ። ይህም እጅግ የተቀደሰ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ የኃጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአቱ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ይታረዳል፤ እርሱ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 6:25
13 Referências Cruzadas  

እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በልዩ ስፍራ አን​ጻር በሰ​ሜ​ንና በደ​ቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነ​ርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ካህ​ናቱ ከሁሉ ይልቅ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ምግብ የሚ​በ​ሉ​ባ​ቸው ቤቶች ናቸው። ስፍ​ራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር፥ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንና የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት ያኖ​ራሉ።


በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አጠ​ገብ በመ​ስዕ በኩል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ዱ​ታል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


“መባ​ውም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን ያቀ​ር​ባል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት እን​ዲ​ኖ​ረው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል።


በሬ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ ደሙን ያቀ​ር​ባሉ፤ ደሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል።


የቅ​ዱ​ሱ​ንና የቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳ​ኑን የአ​ም​ላ​ኩን መባ ይብላ፤


በፍ​የ​ሉም ራስ ላይ እጁን ይጭ​ናል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል፤ እርሱ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።


እጁ​ንም በኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት እን​ስ​ሳ​ትን በሚ​ያ​ር​ዱ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ፍየ​ል​ዋን ያር​ዳ​ታል።


በእ​ርሾ ቦክቶ አይ​ጋ​ገ​ርም። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሰ​ጠ​ኋ​ቸው ዕድል ፈንታ ይህ ነው፤ እር​ሱም እንደ ኀጢ​አ​ትና እንደ በደል መሥ​ዋ​ዕት ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦


ከካ​ህ​ናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከእ​ርሱ ይበ​ላል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት እንደ ሆነ እን​ዲሁ የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ነው፤ ለሁ​ለቱ አንድ ሕግ ነው፤ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ካህን ይወ​ስ​ደ​ዋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios