Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 27:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ለግ​ምቱ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውን ቢያጣ ግን በካ​ህኑ ፊት ይቁም፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለ​ውን ሰው ከእጁ ባለው ገን​ዘብ መጠን ይገ​ም​ት​ለት፤ ካህ​ኑም የተ​ሳ​ለው ሰው እን​ደ​ሚ​ችል መጠን ይገ​ም​ት​ለት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስእለት የተሳለው ድኻ ከሆነና ግምቱን መክፈል ካልቻለ ግን፣ ለስጦታ ያሰበውን ሰው ወደ ካህኑ ያምጣ፤ ካህኑም የተሳለው ሰው ባለው ዐቅም መሠረት መክፈል የሚገባውን ይተምንለታል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ማናቸውም ሰው ለግምትህ ከድህነቱ የተነሣ የሚከፍለውን ቢያጣ እርሱም በካህኑ ፊት የስለቱን ሰው የምጣው፥ ካህኑም እርሱን ይገምተው፤ ካህኑም የተሳለው ሰው አቅሙ እንደሚፈቅደው መጠን ይገምትለት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “ስእለት ያደረገው ሰው ይህን ተመን ለመክፈል የማይችል ሆኖ ከተገኘ ያ ለስጦታ የቀረበውን ሰው ወደ ካህኑ ያምጣው፤ ካህኑም ያ ሰው የሚችለውን ያኽል ገምቶ ዝቅተኛ ዋጋ ያስከፍለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ለግምቱም የሚከፍለውን ቢያጣ ግን በካህኑ ፊት ይቁም፥ ካህኑም የተሳለውን ሰው ይገምተው፤ ካህኑም የተሳለው ሰው እንደሚችል መጠን ይገምተው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 27:8
11 Referências Cruzadas  

በጨ​ለ​ማም ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር ይሄዱ ዘንድ ተነሡ፤ ወደ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ሰፈር መጀ​መ​ሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በዚያ ማንም ሰው አል​ነ​በ​ረም።


“ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች በየ​ት​ኛው ይቅር እል​ሻ​ለሁ? ልጆ​ችሽ ትተ​ው​ኛል፤ አማ​ል​ክ​ትም ባል​ሆኑ ምለ​ዋል፤ አጠ​ገ​ብ​ኋ​ቸ​ውም፤ እነ​ርሱ ግን አመ​ነ​ዘሩ፤ በአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዎ​ቹም ቤት ዐደሩ።


ጠቦት ለማ​ም​ጣት የሚ​በቃ ገን​ዘብ በእ​ጅዋ ባይ​ኖ​ራት ሁለት ዋኖ​ሶች፥ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ሌላ​ው​ንም ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ለች፤ ካህ​ኑም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ታል፤ እር​ስ​ዋም ትነ​ጻ​ለች።”


ከስ​ድሳ ዓመ​ትም ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ወንድ ቢሆን ግምቱ ዐሥራ አም​ስት ዲድ​ር​ክም፥ ለሴ​ትም ዐሥር ዲድ​ር​ክም ይሁን።


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ የሚ​ያ​ቀ​ር​በው እን​ስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእ​ነ​ዚህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።


“ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ለማ​ም​ጣት ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና ዘይት አያ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም።


“ስለ ሠራው ኀጢ​አት የበግ መግዣ ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው ግን፥ ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል። ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤


ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም።


ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios