Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 27:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እር​ሻው ግን በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ሲወጣ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ እርሻ ይሆ​ናል፤ ርስ​ቱም ለካ​ህኑ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ዕርሻው በኢዮቤልዩ በሚለቀቅበት ጊዜ ለእግዚአብሔር እንደ ተሰጠ ዕርሻ ተቈጥሮ ቅዱስና የካህናቱ ንብረት ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እርሻው ግን በኢዮቤልዩ ነፃ ሲወጣ እንደ እርም ለጌታ የተቀደሰ እርሻ ይሆናል፤ ለካህኑ ርስቱ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ይህ ለቀድሞ ባለቤቱ ለመመለስ የማይችለው መሬትም በተከታዩ በኢዮቤልዩ ዓመት ለእግዚአብሔር የተለየ ቀዋሚ ንብረት እንደ ሆነ ይቀራል፤ እርሱም የካህኑ ድርሻ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እርሻው ግን በኢዮቤልዩ ሲወጣ እንደ እርም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ እርሻ ይሆናል፤ ርስቱ ለካህኑ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 27:21
11 Referências Cruzadas  

“እስከ ሦስት ቀን ድረስ የማ​ይ​መጣ ሁሉ እንደ ሽማ​ግ​ሎ​ችና እን​ዳ​ለ​ቆች ምክር ከብቱ ሁሉ ይበ​ዝ​በዝ፤ እር​ሱም ከም​ር​ኮው ጉባኤ ይለይ” ብሎ ዐዋጅ አስ​ነ​ገረ።


የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕት የን​ስ​ሓ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ይበ​ላሉ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ እርም የሆ​ነው ነገር ሁሉ ለእ​ነ​ርሱ ይሆ​ናል።


አም​ሳ​ኛ​ው​ንም ዓመት ትቀ​ድ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ለሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ነጻ​ነ​ትን ታው​ጃ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለእ​ና​ንተ ኢዮ​ቤ​ልዩ ነው፤ ሰው ሁሉ ወደ ርስ​ቱና ወደ ወገኑ ይመ​ለስ።


ለራ​ሱም ዕዳ​ውን መክ​ፈል ባይ​ችል፥ ሽያጩ በገ​ዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ ይቀ​መጥ፤ በኢ​ዮ​ቤ​ል​ዩም ዓመት ይውጣ፤ እር​ሱም ወደ ርስቱ ይመ​ለስ።


ቅጥር በሌ​ለ​በት መን​ደር ያሉ ቤቶች ግን እንደ እርሻ ይቈ​ጠ​ራሉ፤ ይቤ​ዣሉ፤ በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም ይመ​ለ​ሳሉ።


እር​ሻ​ው​ንም ባይ​ቤ​ዠው፥ ወይም ለሌላ ሰው ቢሸጥ እንደ ገና ይቤ​ዠው ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ውም።


ከር​ስቱ እርሻ ያል​ሆ​ነ​ውን የገ​ዛ​ውን እርሻ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢሳል፥


በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የተ​ከ​ለ​ከ​ለው ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ቍጣ ይመ​ለስ ዘንድ፥ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም እንደ ማለ​ላ​ቸው ይም​ርህ ዘንድ፥ ይራ​ራ​ል​ህም ዘንድ፥ ያበ​ዛ​ህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆ​ነው አን​ዳች ነገር በእ​ጅህ አት​ንካ።


ከተ​ማ​ዪ​ቱም በእ​ር​ስ​ዋም ያለው ሁሉ ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርም ይሆ​ናሉ፤ የላ​ክ​ና​ቸ​ውን መል​እ​ክ​ተ​ኞች ስለ ሸሸ​ገች ዘማ​ዊቱ ረዓብ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር በቤቷ ውስጥ ያሉ ሁሉ ብቻ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios