Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 26:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 “በሥ​ር​ዐቴ ብት​ሄዱ፥ ትእ​ዛ​ዛ​ቴ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ብታ​ደ​ር​ጉ​ትም፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “ ‘በሥርዐቴ ብትሄዱ፣ ትእዛዜንም በጥንቃቄ ብትጠብቁ፣

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 “በሥርዓቶቼ ብትመላለሱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉአቸውም፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “በሕጌ ብትመሩና ትእዛዞቼንም ብትጠብቁ፥

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በሥርዓቴ ብትሄዱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉትም፥

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 26:3
19 Referências Cruzadas  

ወደ እኔ ብት​መ​ለሱ ግን፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ብታ​ደ​ር​ጓ​ትም ምንም ከእ​ና​ንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢበ​ተኑ፥ ከዚያ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስሜም ይኖ​ር​በት ዘንድ ወደ መረ​ጥ​ሁት ስፍራ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ል​ካ​ለህ፤ እኔ እህ​ል​ህ​ንና ወይ​ን​ህን፥ ውኃ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤ በሽ​ታ​ንም ከአ​ንተ አር​ቃ​ለሁ።


እሽ ብት​ሉና ብት​ሰ​ሙኝ የም​ድ​ርን በረ​ከት ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤


በም​ድ​ርም ለተ​ዘ​ራው ዘርህ ዝናም ይዘ​ን​ማል፤ ከም​ድ​ርም ፍሬ የሚ​ወጣ እን​ጀራ ወፍ​ራ​ምና ብዙ ይሆ​ናል። በዚ​ያም ቀን ከብ​ቶ​ችህ በሰ​ፊና በለ​መ​ለመ መስክ ይሰ​ማ​ራሉ፤


ከግ​ብፅ ሀገር ከብ​ረት ምድጃ ባወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ያዘ​ዝ​ሁ​ትን፥ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ርጉ፤ እን​ዲ​ሁም እና​ንተ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ” ያል​ሁ​ትን ቃሌን ስሙ።


በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ፍሬ​ውን ብሉ፤ ፍሬ​ውም ይበ​ዛ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፣ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፣ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ይህ​ችን ፍርድ ሰም​ታ​ችሁ ብት​ጠ​ብ​ቋት፥ ብታ​ደ​ር​ጓ​ትም፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳ​ንና ምሕ​ረት ለእ​ና​ንተ ይጠ​ብ​ቅ​ላ​ች​ኋል፤


ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios