Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 26:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ብዙ ጊዜ የተ​ቀ​መ​ጠ​ውን፥ የከ​ረ​መ​ው​ንም እህል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ አዲ​ሱ​ንም ታስ​ገቡ ዘንድ የከ​ረ​መ​ውን ታወ​ጣ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የዓምናውን እህል እየበላችሁ ከጐተራው ሳያልቅ ለዘንድሮው እህል ደግሞ ቦታ ታስለቅቃላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለብዙም ጊዜ በጎተራ የተቀመጠውን ቀድሞ የነበረውን እህል ትበላላችሁ፤ ለአዲሱም ቦታ ለማስለቀቅ ቀድሞ በጎተራ የነበረውን ታወጣላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ገና ያለፈውን ሰብል በመብላት ላይ እያላችሁ፥ ለአዲሱ ሰብል ቦታ ማስለቀቅ ይኖርባችኋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ብዙ ጊዜ የተቀመጠውንም አሮጌውን እህል ትበላላችሁ፤ ከአዲሱም በፊት አሮጌውን ታወጣላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 26:10
5 Referências Cruzadas  

“ይህም ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በዚህ ዓመት የገ​ቦ​ውን፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከገ​ቦው የበ​ቀ​ለ​ውን ትበ​ላ​ለህ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ለህ፤ ታጭ​ድ​ማ​ለህ፥ ወይ​ንም ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ፍሬ​ው​ንም ትበ​ላ​ለህ።


ዐው​ድ​ማ​ዎ​ችም እህ​ልን ይሞ​ላሉ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ዎ​ችም የወ​ይን ጠጅ​ንና ዘይ​ትን አት​ረ​ፍ​ር​ፈው ያፈ​ስ​ሳሉ።


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ዓመት ትዘ​ራ​ላ​ችሁ፤ ከከ​ረ​መ​ውም እህል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ፍሬዋ እስ​ኪ​ገባ፥ እስከ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመት ድረስ፥ ከከ​ረ​መው እህል ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


እህ​ሌን የማ​ኖ​ር​በት የለ​ኝ​ምና ምን ላድ​ርግ ብሎ በልቡ ዐሰበ።


ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚ​ያው ቀን በሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios