Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 25:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “ሥር​ዐ​ቴ​ንም አድ​ርጉ፤ ፍር​ዴ​ንም ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ውስጥ ተዘ​ል​ላ​ችሁ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ ‘ሥርዐቴን ጠብቁ፤ ሕጌን በጥንቃቄ አድርጉ፤ በምድሪቱም ያለ ሥጋት ትኖራላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “ሥርዓቶቼን አድርጉ፥ ፍርዴንም ጠብቁ አድርጉትም፤ በምድሪቱም ላይ በደኅንነት ትቀመጣላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “በምድሪቱ ላይ በሰላም ትኖሩ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አክብሩ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሥርዓቴንም አድርጉ፥ ፍርዶቼንም ጠብቁ አድርጉትም፤ በምድሪቱም ውስጥ በጸጥታ ትኖራላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 25:18
20 Referências Cruzadas  

እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት፦ በአ​ንተ ፋንታ በዙ​ፋ​ንህ ላይ የማ​ስ​ቀ​ም​ጠው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል ብሎ እንደ ነገ​ረው፥ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ አስ​ባ​ለሁ።


ረጃ​ጅም ተራ​ራ​ዎች ለዋ​ሊ​ያ​ዎች፥ ድን​ጋ​ዮ​ችም ለአ​ሽ​ኮ​ኮ​ዎች መሸሻ ናቸው።


በእ​ርሱ በሰ​ላም እተ​ኛ​ለሁ፥ አን​ቀ​ላ​ፋ​ለ​ሁም፤ አቤቱ፥አንተ ብቻ​ህን በተ​ስፋ አሳ​ድ​ረ​ኸ​ኛ​ልና።


የሚሰማኝ ግን በተስፋ ይኖራል፥ ከክፉም ሁሉ ያለ ድንጋጤ ያርፋል።”


በዘ​መ​ኑም ይሁዳ ይድ​ናል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ተዘ​ልሎ ይቀ​መ​ጣል፤ ይህም ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያት ኢዮ​ሴ​ዴቅ ብሎ የጠ​ራው ነው።


እር​ሱም፥ “ሁላ​ችሁ እና​ንተ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ች​ሁና ከሥ​ራ​ችሁ ክፋት ተመ​ለሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ጣ​ችሁ ምድር ትቀ​መ​ጣ​ላ​ችሁ አለ።


በዚ​ያም ዘመን ይሁዳ ይድ​ናል፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተዘ​ልላ ትቀ​መ​ጣ​ለች፤ የም​ት​ጠ​ራ​በ​ትም ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቃ​ችን ተብሎ ነው።


ስላ​ደ​ረ​ጉ​ትም ርኵ​ሰት ሁሉ ምድ​ሪ​ቱን ባድ​ማና ውድማ ባደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


“ሥር​ዐ​ቴን ጠብቁ፤ በበ​ሬህ በባ​ዕድ ቀን​በር አት​ረስ፤ በወ​ይን ቦታህ የተ​ለ​ያየ ዘር አት​ዝራ፤ ከሁ​ለት ዐይ​ነት ነገር የተ​ሠራ ልብስ ኀፍ​ረት ነውና አት​ል​በስ።


ሕጌን ሁሉ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”


ምድ​ሪ​ቱም ፍሬ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ግ​ቡም ድረስ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ውስጥ ተዘ​ል​ላ​ችሁ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


ዮር​ዳ​ኖ​ስን ግን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ያ​ወ​ር​ሳ​ችሁ ምድር በተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥ ያለ ፍር​ሀ​ትም እን​ድ​ት​ኖሩ ከከ​በ​ቡ​አ​ችሁ ጠላ​ቶች ሁሉ ዕረ​ፍት በሰ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥


ስለ ብን​ያ​ምም እን​ዲህ አለ፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ወ​ደደ በእ​ርሱ ዘንድ ተማ​ምኖ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዘ​መኑ ሁሉ ይጋ​ር​ደ​ዋል፤ በት​ከ​ሻ​ውም መካ​ከል ያድ​ራል።


እስ​ራ​ኤ​ልም ተማ​ምኖ፥ በያ​ዕ​ቆብ ምድር ብቻ​ውን፥ በስ​ን​ዴና በወ​ይን ምድር ይኖ​ራል፤ ሰማይ ከደ​መ​ናና ከጠል ጋር ለአ​ንተ ነው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios