Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 24:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለሀ​ገር ልጅ አንድ ዐይ​ነት ሕግ ይሁ​ን​ላ​ችሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ለመጻተኛው ሆነ ለአገር ተወላጅ አንድ ዐይነት ሕግ ይኑራችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና ለመጻተኛና ለአገሩ ተወላጅ አንድ ዓይነት ሕግ ይኑራችሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ይህም ሕግ ለሁላችሁም ማለትም ለእናንተ ለእስራኤላውያንም ሆነ፥ በእናንተ መካከል ለሚኖሩት መጻተኞች ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለመጻተኛና ለአገር ልጅ አንድ ዓይነት ሕግ ይሁንላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 24:22
8 Referências Cruzadas  

ለሀ​ገር ልጅ፥ በእ​ና​ንተ መካ​ከ​ልም ለሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል።”


“ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚ​በ​ላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ያንም ሰው ከሕ​ዝቡ ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤ ወደ እና​ንተ የመጣ እን​ግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ እር​ሱን እንደ ራሳ​ችሁ ውደ​ዱት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


ሙሴም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ተሳ​ዳ​ቢ​ው​ንም ከሰ​ፈር ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ በድ​ን​ጋ​ይም ወገ​ሩት። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።


ትው​ልዱ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ቢሆን፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው የሚ​ኖር መጻ​ተኛ ቢሆን፥ ሳያ​ውቅ ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆ​ን​ለ​ታል።


ወደ አገ​ራ​ችሁ መጻ​ተኛ ቢመጣ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ እንደ ፋሲ​ካው ሕግ እንደ ትእ​ዛ​ዙም ያድ​ርግ፤ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለሀ​ገር ልጅ አንድ ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።”


በዚ​ያን ጊዜ ፈራ​ጆ​ቻ​ች​ሁን አዘ​ዝ​ኋ​ቸው። አል​ኋ​ቸ​ውም፦ የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ነገር ስሙ፤ በሰ​ውና በወ​ን​ድሙ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ባለው መጻ​ተኛ መካ​ከል በጽ​ድቅ ፍረዱ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios