Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 23:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ እና​ንተ ማስ​ተ​ስ​ረያ ትሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ የማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ቀን ናትና በዚ​ያች ቀን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ለእናንተ ስርየት የሚደረግበት የስርየት ቀን ስለ ሆነ፣ በዚያ ዕለት ምንም ሥራ አትሥሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በአምላካችሁም በጌታ ፊት ማስተስረያ እንዲሆንላችሁ የማስተስረያ ቀን ነውና በዚያ ቀን ሥራ ሁሉ አትሥሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት የሕዝቡን ኃጢአት የማስወገድ ሥርዓት የሚፈጸምበት ዕለት ስለ ሆነ፥ በዚያን ቀን ምንም ሥራ አትሥሩበት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ፊት ማስተስረያ ይሆንላችሁ ዘንድ የማስተስረያ ቀን ነውና በዚያ ቀን ሥራ ሁሉ አትሥሩ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 23:28
15 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።


በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስ​ተ​ስ​ረያ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋ​ልና በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ራሳ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቋት፤ የሀ​ገር ልጅም፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል የተ​ቀ​መጠ እን​ግዳ ሥራን ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ።


ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ንም ያስ​ተ​ስ​ርይ፤ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን፥ ለመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ያስ​ተ​ስ​ርይ፤ ለካ​ህ​ና​ቱም፥ ለጉ​ባ​ኤ​ውም ሕዝብ ሁሉ ያስ​ተ​ስ​ርይ።


ይህም አንድ ጊዜ በዓ​መት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አደ​ረገ።


“በዚህ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ዐሥ​ረ​ኛዋ ቀን የማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ቀን ናት፤ ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቋት፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ።


በኢያሱ ፊት ያኖርሁት ድንጋይ እነሆ አለ፣ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፣ እነሆ፥ ቅርጹን እቀርጻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።


በፈ​ቃ​ዱም አንድ ጊዜ በተ​ደ​ረ​ገው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሥ​ጋዉ ቍር​ባን ተቀ​ደ​ስን።


ለሚ​ቀ​ደ​ሱ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የም​ት​ሆን አን​ዲት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ።


የዘ​ለ​ዓ​ለም መድ​ኀ​ኒ​ትን ገን​ዘብ አድ​ርጎ፥ በገዛ ደሙ አንድ ጊዜ ወደ መቅ​ደስ ገባ እንጂ በላ​ምና በፍ​የል ደም አይ​ደ​ለም።


ይህስ ባይ​ሆን ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ በሞተ ነበር፤ አሁን ግን በዓ​ለም ፍጻሜ፥ ራሱን በመ​ሠ​ዋት ኀጢ​አ​ትን ይሽ​ራት ዘንድ አንድ ጊዜ ተገ​ለጠ።


እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።


ፍቅርም እንደዚህ ነው። እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።


በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios