Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 23:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ካህ​ኑም ከበ​ኵ​ራቱ ኅብ​ስት፥ ከሁ​ለ​ቱም ጠቦ​ቶች ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለቍ​ር​ባን ያቅ​ር​በው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ፈንታ ነው፤ ላቀ​ረ​በው ለካ​ህኑ ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ካህኑም ሁለቱን የበግ ጠቦቶች ከበኵራቱ እንጀራ ጋራ የሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ እነዚህም ለእግዚአብሔር ቅዱስ መሥዋዕት፣ የካህኑም ድርሻ ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ካህኑም ከበኩራቱ እንጀራ ከሁለቱም ጠቦቶች ጋር በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ይወዘውዛቸዋል። ለካህኑ ለጌታ የተቀደሱ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ካህኑም ከበኲራቱ እንጀራ ከሁለቱ ጠቦቶች ጋር በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቀርባል፤ እርሱም የካህናቱ ድርሻ ሆኖ ይነሣል፤ እነዚህም ስጦታዎች የተቀደሱ ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ካህኑም ከበኵራቱ እንጀራ ከሁለቱም ጠቦቶች ጋር በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ይወዘውዛቸዋል፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ፈንታ ነው፤ ለካህኑ ይሁን።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 23:20
12 Referências Cruzadas  

ሁሉ​ንም በአ​ሮን እጆ​ችና በል​ጆቹ እጆች ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ።


ከየ​ማ​ደ​ሪ​ያ​ችሁ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት የተ​ሠራ ሁለት የቍ​ር​ባን እን​ጀራ ታመ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ህ​ላ​ችሁ ቀዳ​ም​ያት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሾ ይጋ​ገ​ራል።


አን​ድም አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ሁለ​ትም የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦ​ቶች ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው የእ​ህል ቍር​ባን ጋር ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ።


ያች​ንም ቀን ቅድ​ስት ጉባኤ ብላ​ችሁ ታው​ጃ​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባር ሥራ ሁሉ አታ​ድ​ር​ጉ​ባት፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​በት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።


ሙሴም ከቅ​ድ​ስ​ናው አውራ በግ ፍር​ም​ባ​ውን ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በው ዘንድ ቈራ​ረጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ይህ ለቅ​ድ​ስና ከታ​ረ​ደው አውራ በግ የሙሴ እድል ፈንታ ሆነ።


“ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት፥ ሰላ​ምም በም​ድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር።


እኛ መን​ፈ​ሳ​ዊ​ውን ነገር ከዘ​ራ​ን​ላ​ችሁ ሥጋ​ዊ​ውን ነገር ብና​ጭድ ታላቅ ነገር ነውን?


ሁለ​ቱን አንድ ያደ​ረገ ሰላ​ማ​ችን እርሱ ነውና፥ በሥ​ጋ​ውም በመ​ካ​ከል የነ​በ​ረ​ውን የጥል ግድ​ግዳ አፍ​ርሶ ጥልን ሻረ።


የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይ​ን​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ አስ​ቀ​ድ​ሞም የተ​ሸ​ለ​ተ​ውን የበ​ግ​ህን ጠጕር ለእ​ርሱ ትሰ​ጣ​ለህ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios