Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 19:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “በፍ​ርድ ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ፤ ለድሃ አታ​ድላ፤ ባለ​ጠ​ጋ​ው​ንም አታ​ክ​ብር፤ ነገር ግን ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ በእ​ው​ነት ፍረድ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “ ‘ፍርድ አታዛቡ፤ ለድኻው አታድላለት፤ ለትልቁም ሰው ልዩ አክብሮት አትስጥ፤ ለብርቱው አታድላ፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በጽድቅ ፍረድ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “ፍርድን ፈጽሞ አታጓድሉ፤ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በጽድቅ ፍረድ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በፍርድ ዓመፃ አታድርጉ፤ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በእውነት ፍረድ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 19:15
20 Referências Cruzadas  

ከእ​ርሱ ወደ ኋላ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ች​ሁን? እስኪ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።


ከሰው የተ​ነሣ አላ​ፍ​ር​ምና፥ ከሟች ሰውም የተ​ነሣ አላ​ፈ​ገ​ፍ​ግ​ምና።


እርሱ ግን የክ​ቡ​ርን ሰው ፊት አያ​ፍ​ርም። ለታ​ላ​ቁም ክብር መስ​ጠ​ትን አያ​ው​ቅም፥ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አይ​ሸ​ሽም።


እነሆ፥ ጠላ​ቶ​ችህ ጮኸ​ዋ​ልና፥ ጠላ​ቶ​ች​ህም ራሳ​ቸ​ውን አን​ሥ​ተ​ዋ​ልና።


አን​ተም ከሕ​ዝቡ ሁሉ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን እው​ነ​ተ​ኞች ሰዎ​ችን፥ ትዕ​ቢ​ት​ንም የሚ​ጠሉ ሰዎ​ችን ፈልግ። ከእ​ነ​ር​ሱም የሺህ አለ​ቆ​ችን፥ የመቶ አለ​ቆ​ችን፥ የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችን፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆ​ችን ሹም​ላ​ቸው።


የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም። በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥


የነገሩትን የሚጠብቅ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የሚቀበልም እርሱን ይቀበለዋል።


“በፍ​ርድ፥ በመ​ለ​ካ​ትም፥ በመ​መ​ዘ​ንም፥ በመ​ስ​ፈ​ርም ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ።


የእ​ው​ነት ፍርድ ፍረዱ እንጂ ለሰው ፊት በማ​ድ​ላት አት​ፍ​ረዱ።”


ጳው​ሎ​ስም መልሶ፥ “አንተ የተ​ለ​ሰነ ግድ​ግዳ በሕግ ልት​ፈ​ር​ድ​ብኝ ተቀ​ም​ጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝ​ዛ​ለ​ህን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ሃል” አለው።


በፍ​ር​ድም ፊት አትዩ፤ ለት​ል​ቁም፥ ለት​ን​ሹም በእ​ው​ነት ፍረዱ፤ ለሰው ፊት አታ​ድሉ፤ ፍርድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። አንድ ነገር ቢከ​ብ​ዳ​ችሁ እር​ሱን ወደ እኔ አም​ጡት፤ እኔም እሰ​ማ​ዋ​ለሁ፤


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ፥ የጌ​ቶች ጌታ፥ ታላቅ አም​ላክ፥ ኀያ​ልም፥ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራም፥ በፍ​ር​ድም የማ​ያ​ደላ፥ መማ​ለ​ጃም የማ​ይ​ቀ​በል ነውና።


ፍር​ድን አታ​ጣ​ምም፤ ፊት አይ​ተ​ህም አታ​ድላ፤ ጉቦን አት​ቀ​በል፥ ጉቦ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ቃል ያጣ​ም​ማ​ልና ጉቦ አት​ቀ​በል።


“በመ​ጻ​ተኛ፥ በድሃ-አደ​ጉም፥ በመ​በ​ለ​ቲ​ቱም ላይ ፍር​ድን የሚ​ያ​ጣ​ምም ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios