Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 15:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “ሴትም ከግ​ዳ​ጅዋ ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈ​ስስ፥ ወይም ደምዋ ከግ​ዳ​ጅዋ ወራት በኋላ ቢፈ​ስስ፥ በግ​ዳ​ጅዋ ወራት እንደ ሆነች እን​ዲሁ በፈ​ሳ​ሽዋ ርኩ​ስ​ነት ወራት ትሆ​ና​ለች፤ ርኵ​ስት ናት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “ ‘ሴት ከወር አበባዋ ጊዜ ሌላ ብዙ ቀን ደም ቢፈስሳት፣ ወይም የወር አበባዋ ጊዜ ካለፈ በኋላ የደሙ መፍሰስ ባይቋረጥ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ፣ ደም መፍሰሱ እስኪቆም ድረስ ርኩስ ትሆናለች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “አንዲትም ሴት ከወር አበባዋ ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፥ ወይም ደምዋ ከወር አበባዋ ጊዜያት የሚበልጥ ቢፈስስ፥ ፈሳሹ ነገር በሚፈስስበት ቀን ሁሉ በርኩስነትዋ ትቀጥላለች፤ በወር አበባዋ ጊዜያት እንደ ሆነች እንዲሁ እርሷ ርኩስ ትሆናለች።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “አንዲት ሴት ከወር አበባዋ ወቅት አልፎ ለብዙ ቀን የሚፈስ ወይም ከተመደበው የወር አበባዋ በኋላ ባለማቋረጥ የሚፈስ ደም ቢኖራት፥ ደሙ እስከሚቆምበት ጊዜ ድረስ ልክ በወር አበባዋ ጊዜ እንደ ነበረችበት ሁኔታ የረከሰች ትሆናለች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሴትም ከመርገም ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፥ ወይም ደምዋ ከመርገምዋ ወራት የሚበልጥ ቢፈስስ፥ በመርገምዋ ወራት እንደ ሆነች እንዲሁ በፈሳሽዋ ርኵስነት ወራት ትሆናለች፤ ርኩስ ናት።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 15:25
6 Referências Cruzadas  

ደም​ዋም በሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ወራት ሁሉ የም​ት​ተ​ኛ​በት መኝታ ሁሉ በግ​ዳ​ጅዋ ጊዜ እንደ ነበ​ረው መኝታ ያለ ይሆ​ን​ባ​ታል፤ የም​ት​ቀ​መ​ጥ​በት ነገር ሁሉ እንደ ግዳ​ጅዋ ርኩ​ስ​ነት ርኩስ ነው።


እነሆም ከዐሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤


ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios