Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ካህ​ኑም በሥ​ጋው ቆዳ ያለ​ች​ውን ያችን ደዌ ይያት፤ ጠጕ​ሯም ተለ​ውጣ ብት​ነጣ በሥ​ጋው ቆዳ ያለች የዚ​ያች ደዌ መልክ ቢከፋ፥ ደዌ​ውም ወደ ሥጋው ቆዳ ቢጠ​ልቅ፥ እር​ስዋ የለ​ምጽ ደዌ ናት፤ ካህ​ኑም አይቶ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይበ​ለው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ካህኑም በሰውየው ቈዳ ላይ ያለውን ቍስል ይመርምር፤ በቍስሉ በተበከለው አካባቢ ያለው ጠጕር ወደ ነጭነት ተለውጦ ቢያገኘውና ቦታው ጐድጕዶ ወደ ውስጥ ቢገባ፣ ይህ ተላላፊ የቈዳ በሽታ ነው። ካህኑም መርምሮ ይህን ባወቀ ጊዜ፣ ሰውየው በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ርኩስ መሆኑ ይገለጽ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ካህኑም በሰውነቱ ቆዳ ላይ ያለውን ደዌ ያያል፤ ጠጉሩም ተለውጦ ቢነጣ ደዌውም ከሰውነቱ ቆዳ በታች ዘልቆ ቢታይ፥ እርሱ የለምጽ ደዌ ነው፤ ካህኑም አይቶ፦ ርኩስ ነው ይበለው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ካህኑም ቊስሉን ይመርምር፤ በዚያም ቊስል ላይ ያለው ጠጒር ወደ ነጭነት ቢለወጥ፥ ቊስሉም በዙሪያው ካለው ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ቢገኝ፥ እርሱ የሥጋ ደዌ በሽታ ነው፤ ካህኑም ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ካህኑም በሥጋው ቁርበት ያለውን ደዌ ያያል፤ ጠጉሩም ተለውጦ ቢነጣ ደዌውም ወደ ሥጋው ቁርበት ቢጠልቅ፥ እርሱ የለምጽ ደዌ ነው፤ ካህኑም አይቶ፦ ርኩስ ነው ይበለው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 13:3
29 Referências Cruzadas  

ከአ​ዜብ ባደ​ረ​ገው በጕ​ዞ​ውም ወደ ቤቴል ሄደ፤ ያም ስፍራ አስ​ቀ​ድሞ በቤ​ቴ​ልና በጋይ መካ​ከል ድን​ኳን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረው ነው፤


“ይህን ሁሉ የሴ​ሰኛ ሴት ሥራን ሠር​ተ​ሻ​ልና፥ ከሴ​ቶች ልጆ​ች​ሽም ጋር ሦስት ጊዜ አመ​ን​ዝ​ረ​ሻ​ልና ሴቶች ልጆ​ች​ሽን ምን አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ? ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውና ባል​ተ​ቀ​ደ​ሰው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ሕዝ​ቤን ያስ​ተ​ምሩ፤ ንጹ​ሕና ንጹሕ ባል​ሆ​ነው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ያሳ​ዩ​አ​ቸው።


ጠላት ጕል​በ​ቱን በላው፤ እርሱ ግን አላ​ወ​ቀም፤ ሽበ​ትም ወጣ​በት፤ እር​ሱም ገና አላ​ስ​ተ​ዋ​ለም።


በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውና በአ​ል​ተ​ቀ​ደ​ሰው፥ በር​ኩ​ሱና በን​ጹ​ሑም መካ​ከል ትለ​ያ​ላ​ችሁ፤


ካህ​ኑም ያየ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ በቆ​ዳው ላይ ነጭ እባጭ ቢሆን፥ ጠጕ​ሩም ተለ​ውጦ ቢነጣ፥ ሥጋ​ውም በእ​ባጩ ውስጥ ቢያዥ፥


“ሰው በሥ​ጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብት​ወ​ጣ​በት፥ ብት​ነ​ጣም፥ በሥ​ጋ​ውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብት​መ​ስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካ​ህ​ናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያም​ጡት።


ካህ​ኑም ያያል፤ እነ​ሆም፥ ወደ ቆዳው ውስጥ ጠልቆ ቢታይ፥ ጠጕ​ሩም ተለ​ውጦ ቢነጣ፥ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነው፤ ከቍ​ስሉ ውስጥ ወጥ​ቶ​አል።


ቋቍ​ቻ​ውም በሥ​ጋው ቆዳ ላይ ቢነጣ፥ ከቆ​ዳ​ውም የጠ​ለቀ ባይ​መ​ስል፥ ጠጕ​ሩም ባይ​ነጣ፥ ካህኑ የታ​መ​መ​ውን ሰው ሰባት ቀን ይዘ​ጋ​በ​ታል።


ካህ​ኑም ያያል፤ እነ​ሆም፥ ምል​ክቱ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ ለምጽ ነውና።


የለ​ም​ጹ​ንም ምል​ክት ያያል፤ እነ​ሆም፥ የለ​ምጹ ምል​ክት በግ​ንቡ ላይ በአ​ረ​ን​ጓ​ዴና በቀይ ቢዥ​ጐ​ረ​ጐር፥ መል​ኩም ወደ ግንቡ ውስጥ ቢጠ​ልቅ፥


“ይህም ሕግ ነው፤ ለሁሉ ዓይ​ነት ለም​ጽና የቈ​ረ​ቈር ደዌ ሕጉ ይህ ነው፤


ለዕ​ባ​ጭም፥ ለብ​ጕ​ርም፥ ለቋ​ቍ​ቻም፤


ወይም ርኩ​ስ​ነ​ቱን ሳያ​ውቅ ርኩ​ስን ሰው ቢነካ፥ በማ​ና​ቸ​ውም ርኵ​ሰት ቢረ​ክስ፥ ነገሩ በታ​ወቀ ጊዜ በደል ይሆ​ን​በ​ታል።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ካህናቱን ስለ ሕጉ ጠይቅ፣


ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።


የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።”


ኀጢ​ኣ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ያላ​ች​ሁ​ላ​ቸው ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይቅር ያላ​ላ​ች​ኋ​ቸው ግን አይ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ውም።”


አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ኦሪት ኀጢ​አት ናትን? አይ​ደ​ለ​ችም፤ ነገር ግን ኦሪት ባት​ሠራ ኀጢ​አ​ትን ባላ​ወ​ቅ​ኋ​ትም ነበር፤ ኦሪት፥ “አት​መኝ” ባትል ኖሮም ምኞ​ትን ፈጽሞ ባላ​ወ​ቅ​ኋ​ትም ነበር።


ከእነዚያም እንዳይሳደቡ ይማሩ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ናቸው።


ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች እያሳቱና እየሳቱ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የነ​ገ​ሩ​አ​ች​ሁን መም​ህ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ዐስቡ፤ መል​ካም ጠባ​ያ​ቸ​ውን አይ​ታ​ችሁ በእ​ም​ነት ምሰ​ሉ​አ​ቸው።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios