Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘሌዋውያን 13:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ያየ​ዋል፤ በቆ​ዳ​ውም ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነውና በእ​ት​ራቱ ላይ ወጥ​ቶ​አል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በሰባተኛው ቀን ካህኑ ይመርምረው፤ በሽታውም በቈዳው ላይ ተስፋፍቶ ቢያገኘው፣ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ፤ ተላላፊ የቈዳ በሽታ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ያየዋል፤ በቆዳውም ላይ ቢስፋፋ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በሰባተኛውም ቀን ካህኑ እንደገና ይመርምረው፤ ቊስሉ ተስፋፍቶ ከተገኘ የሥጋ ደዌ በሽታ ነው፤ ስለዚህም ያ ሰው የረከሰ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ካህኑም በሰባተኛው ቀን ያየዋል፤ በቁርበቱም ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘሌዋውያን 13:27
6 Referências Cruzadas  

“ሰው በሥ​ጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብት​ወ​ጣ​በት፥ ብት​ነ​ጣም፥ በሥ​ጋ​ውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብት​መ​ስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካ​ህ​ናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያም​ጡት።


ካህ​ኑም ቢያ​የው፥ በቋ​ቍ​ቻ​ውም ነጭ ጠጕር ባይ​ኖር፥ ወደ ቆዳ​ውም ባይ​ጠ​ልቅ፥ ነገር ግን ቢከ​ስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።


ቋቍ​ቻ​ውም በስ​ፍ​ራው ላይ ቢቆም፥ በቆ​ዳ​ውም ላይ ባይ​ሰፋ፥ ነገር ግን ቢከ​ስም፥ የት​ኩ​ሳት እባጭ ነው፤ የት​ኩ​ሳ​ትም ጠባሳ ነውና ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለ​ዋል።


ከነጻ በኋላ ግን ቈረ​ቈሩ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ያየ​ዋል፤


ስለ መን​ጻቱ በካ​ህኑ ዘንድ ከታየ በኋላ ምል​ክቱ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ፥ እን​ደ​ገና ሊታይ ወደ ካህኑ ይቀ​ር​ባል።


ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ተመ​ልሶ ቤቱን ያያል፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios