Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሰቈቃወ 3:66 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

66 አቤቱ፥ እንደ ልባ​ቸው ክፋት በቍ​ጣህ ታሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ማ​ይም በታች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

66 ከእግዚአብሔር ሰማያት በታች፣ በቍጣህ አሳድዳቸው፤ አጥፋቸውም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

66 አቤቱ፥ በቁጣ ታሳድዳቸዋለህ ከሰማይም በታች ታጠፋቸዋለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

66 እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አሳዳቸው፤ ከሰማያትም በታች ደምስሳቸው!”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

66 አቤቱ፥ በቍጣ ታሳድዳቸዋለህ ከሰማይም በታች ታጠፋቸዋለህ።

Ver Capítulo Cópia de




ሰቈቃወ 3:66
14 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ዘር ከሰ​ማይ በታች ይደ​መ​ስስ ዘንድ አል​ተ​ና​ገ​ረም፤ ነገር ግን በዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እጅ አዳ​ና​ቸው።


አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ በሰ​ማይ ነው፥ እው​ነ​ት​ህም እስከ ደመ​ናት ትደ​ር​ሳ​ለች።


ጽድ​ቅ​ህም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራ​ሮች ናት፤ ፍር​ድ​ህም እጅግ ጥልቅ ናት።


አንተ ፈሳ​ሾ​ቹ​ንና ምን​ጮ​ቹን ሰነ​ጠ​ቅህ።


የጣ​ቶ​ች​ህን ሥራ ሰማ​ዮ​ችን፥ አንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸ​ውን፥ ጨረ​ቃ​ንና ከዋ​ክ​ብ​ትን እና​ያ​ለ​ንና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ የም​ት​ሠ​ሩ​ልኝ ቤት ምን ዓይ​ነት ነው? የማ​ር​ፍ​በ​ትስ ስፍራ ምን​ድን ነው?


እና​ን​ተም፦ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ያል​ፈ​ጠሩ እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ከም​ድር ላይ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ፈጽ​መው ይጥፉ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።


አቤቱ! አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ አስ​በኝ፤ ጐብ​ኘ​ኝም፤ ከሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝም አድ​ነኝ እንጂ፥ አት​ታ​ገ​ሣ​ቸው፤ ስለ አንተ እንደ ሰደ​ቡኝ አስብ።


ሳም​ኬት። በቍ​ጣህ ከደ​ን​ኸን፤ አሳ​ደ​ድ​ኸ​ንም፤ ገደ​ል​ኸን፤ አል​ራ​ራ​ህ​ል​ንም።


እስ​ራ​ኤል ደግ​ነ​ቱን ጥሎ​አ​ልና፤ ጠላ​ትም ያሳ​ድ​ደ​ዋ​ልና።


ስለ​ዚህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከሚ​ከ​ብ​ቡህ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሳ​ረ​ፈህ ጊዜ፥ የዐ​ማ​ሌ​ቅን ዝክረ ስሙን ከሰ​ማይ በታች አጥ​ፋው፤ ይህ​ንም አት​ርሳ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ፥ ቅን​አ​ቱም በዚያ ሰው ላይ ይነ​ድ​ዳል እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ርታ አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም፤ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈው ርግ​ማን ሁሉ በላዩ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ከሰ​ማይ በታች ይደ​መ​ስ​ሰ​ዋል።


ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ስማ​ቸ​ው​ንም ከዚያ ቦታ ያጠ​ፋል፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ማንም ከፊ​ትህ ይቆም ዘንድ አይ​ች​ልም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios