Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መሳፍንት 8:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ለጌ​ዴ​ዎ​ንም ብዙ ሚስ​ቶች ነበ​ሩ​ትና ከአ​ብ​ራኩ የወጡ ሰባ ልጆች ነበ​ሩት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ጌዴዎን ብዙ ሚስቶች ስላገባ ሰባ ልጆች ነበሩት፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ብዙ ሚስቶች ስላገባ ሰባ ልጆች ነበሩት፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ብዙ ሚስቶች ስላገባ ሰባ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ለጌዴዎንም ብዙ ሚስቶች ነበሩትና ከወገቡ የወጡ ሰባ ልጆች ነበሩት።

Ver Capítulo Cópia de




መሳፍንት 8:30
20 Referências Cruzadas  

ስለ​ዚህ ሰው አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ሚስ​ቱ​ንም ይከ​ተ​ላል ፤ ሁለ​ቱም አንድ ሥጋ ይሆ​ናሉ።


ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት ሰዎች ሁሉ ከጕ​ል​በቱ የወ​ጡት፥ ከል​ጆቹ ሚስ​ቶች ሌላ፥ ሁላ​ቸው ስድሳ ሰባት ናቸው።


ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆ​ቹ​ንና ሚስ​ቱን፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ሚስ​ቶች ይዞ ወደ መር​ከብ ገባ።


ለእ​ር​ሱም ሰባት መቶ ሚስ​ቶ​ችና ሦስት መቶ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት።


ለአ​ክ​አ​ብም በሰ​ማ​ርያ ሰባ ልጆች ነበ​ሩት፤ ኢዩም ደብ​ዳቤ ጽፎ፥ የአ​ክ​አ​ብን ልጆች ለሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ ለሰ​ማ​ርያ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ሰማ​ርያ ላከ።


ዮሴ​ፍም አስ​ቀ​ድሞ በግ​ብፅ ነበረ። ከያ​ዕ​ቆብ ጕል​በት የወ​ጡት ሰዎች ሁሉ ሰባ ነፍ​ሶች ነበሩ፤


እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።


ልቡም እን​ዳ​ይ​ስት ሚስ​ቶ​ችን ለእ​ርሱ አያ​ብዛ፤ ወር​ቅና ብርም ለእ​ርሱ እጅግ አያ​ብዛ።


በሠ​ላሳ ሁለት የአ​ህያ ግል​ገ​ሎች ይቀ​መጡ የነ​በሩ ሠላሳ ሁለት ልጆ​ችም ነበ​ሩት፤ ለእ​ነ​ር​ሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች የተ​ባሉ በገ​ለ​ዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተ​ሞች ነበ​ሩ​አ​ቸው።


አር​ባም ልጆች፥ ሠላ​ሳም የልጅ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በሰ​ባም የአ​ህያ ግል​ገ​ሎች ላይ ይቀ​መጡ ነበር። እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስም​ንት ዓመት ገዛ።


ሠላሳ ወን​ዶች ልጆ​ችና ሠላሳ ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለደ፤ ሠላሳ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም ወደ ውጭ ሀገር ዳረ፤ ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቹም ከውጭ ሀገር ሠላሳ ሴቶች ልጆ​ችን አመጣ። እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሰባት ዓመት ገዛ።


በሴ​ኬ​ምም የነ​በ​ረ​ችው ዕቅ​ብቱ ወንድ ልጅ ወለ​ደ​ች​ለት፤ ስሙ​ንም አቤ​ሜ​ሌክ ብሎ ጠራው።


የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ወደ ሰቂማ ወደ እናቱ ወን​ድ​ሞች ሄደ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም፥ ለእ​ናቱ አባት ቤተ ሰቦ​ችም ሁሉ እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፦


እና​ን​ተም ዛሬ በአ​ባቴ ቤት ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል፤ ሰባ የሆ​ኑ​ትን ልጆ​ቹ​ንም በአ​ንድ ድን​ጋይ ላይ ገድ​ላ​ች​ኋል፤ ወን​ድ​ማ​ች​ሁም ስለ​ሆነ የዕ​ቅ​ብ​ቱን ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን በሰ​ቂማ ሰዎች ላይ አን​ግ​ሣ​ች​ኋል፥


“ለሰ​ቂማ ሰዎች ሁሉ፦ ሰባ የሆ​ኑት የይ​ሩ​በ​ኣል ልጆች ሁሉ ቢገ​ዙ​አ​ችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገ​ዛ​ችሁ ምን ይሻ​ላ​ች​ኋል? ብላ​ችሁ ንገ​ሩ​አ​ቸው፤ ደግ​ሞም እኔ የአ​ጥ​ን​ታ​ችሁ ፍላጭ፥ የሥ​ጋ​ችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ።”


ወደ አባ​ቱም ቤት ወደ ኤፍ​ራታ ገባ፤ ሰባ የሆ​ኑ​ትን የይ​ሩ​በ​ኣ​ልን ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ንድ ድን​ጋይ ላይ ገደ​ላ​ቸው፤ ትንሹ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ ኢዮ​አ​ታም ግን ተሸ​ሽጎ ነበ​ርና ተረፈ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios