Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መሳፍንት 7:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጌዴ​ዎ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት መቶ ሰዎች በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው ትጋት መጀ​መ​ሪያ ዘብ ጠባ​ቂ​ዎች ሳይ​ነቁ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ች​ንም ነፉ፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ማሰ​ሮ​ዎች ሰባ​በሩ፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ዘቦቹ ተቀያይረው የእኩለ ሌሊቱን ጥበቃ በጀመሩበት ጊዜ፣ ጌዴዎንና ዐብረውት የነበሩት መቶ ሰዎች በሰፈሩ ዳርቻ ደረሱ፤ እነርሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ የያዟቸውንም ማሰሮዎች ሰበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ዘቦቹ ተቀያይረው የእኩለ ሌሊቱን ጥበቃ በጀመሩበት ጊዜ፥ ጌዴዎንና አብረውት የነበሩት መቶ ሰዎች በሰፈሩ ዳርቻ ደረሱ፤ እነርሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ የያዟቸውንም ማሰሮች ሰበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከእኩለሌሊት ጥቂት ቀደም ብሎ፥ ዘብ ጠባቂዎች ከተቀያየሩ በኋላ ጌዴዎንና ከእርሱ ጋር የተመደቡት መቶ ሰዎች ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ እምቢልታዎቻቸውን ነፉ፤ የያዙትንም ማሰሮ ሁሉ ሰባበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጌዴዎንም ከእርሱም ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች በመካከለኛው ትጋት ትጋቱም በተጀመረ ጊዜ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፥ ቀንደ መለከቶችንም ነፉ፥ በእጃቸውም የነበሩትን ማሰሮች ሰባበሩ።

Ver Capítulo Cópia de




መሳፍንት 7:19
11 Referências Cruzadas  

በብ​ረት በትር ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”


በላ​ባ​ዎቹ ይጋ​ር​ድ​ሃል፥ በክ​ን​ፎ​ቹም በታች ትተ​ማ​መ​ና​ለህ፤ እው​ነት እንደ ጋሻ ይከ​ብ​ብ​ሃል።


ንጋ​ትም በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳ​ትና በደ​መና ዐምድ ሆኖ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ተመ​ለ​ከተ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት አወከ።


እኩል ሌሊትም ሲሆን ‘እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፤ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ፤’ የሚል ውካታ ሆነ።


የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና።


“እነሆ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ ኀፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”


ሦስ​ቱ​ንም መቶ ሰዎች በሦ​ስት ወገን ከፈ​ላ​ቸው፤ በሁ​ሉም እጅ ቀንደ መለ​ከ​ትና ባዶ ማሰሮ፥ በማ​ሰ​ሮ​ዉም ውስጥ ችቦ ሰጣ​ቸው።


እኔ ከእ​ኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለ​ከት ስን​ነፋ፥ እና​ንተ ደግሞ በሰ​ፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለ​ከ​ታ​ች​ሁን ንፉ፦ ኀይል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ሰይፍ የጌ​ዴ​ዎን በሉ” አላ​ቸው።


ሦስ​ቱም ወገ​ኖች ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ነፉ፤ ማሰ​ሮ​ዎ​ች​ንም ሰበሩ፤ በግራ እጃ​ቸ​ውም ችቦ​ዎ​ችን፥ በቀኝ እጃ​ቸ​ውም ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ችን ይዘው እየ​ነፉ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና የጌ​ዴ​ዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios