Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መሳፍንት 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ተነሺ፥ ዲቦራ ሆይ፦ ተነሺ፤ አእ​ላ​ፍን ከሕ​ዝብ ጋር አስ​ነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቅኔ​ው​ንም ተቀኚ፤ ባርቅ ሆይ! በኀ​ይል ተነሣ፤ ዲቦ​ራም ባር​ቅን አጽ​ኚው፥ የአ​ቢ​ኒ​ሔም ልጅ ባር​ቅም ሆይ! ምር​ኮ​ህን ማርክ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤ የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ሆይ፤ ተነሣ፤ ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፥ ባራቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዲቦራ ሆይ! ንቂ! ንቂ! ንቂ! መዝሙርም ዘምሪ! የአቢኒዔም ልጅ ባራቅ ሆይ! ተነሣ! ምርኮህንም እየመራህ ወደ ፊት ገሥግሥ!

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፥ ባርቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ።

Ver Capítulo Cópia de




መሳፍንት 5:12
18 Referências Cruzadas  

የዐ​መ​ፀኛ አፍና የኀ​ጢ​አ​ተኛ አፍ በላዬ ተላ​ቅ​ቀ​ዋ​ልና። በሽ​ን​ገላ አን​ደ​በ​ትም በላዬ ተና​ገሩ፤


እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ ሰም ያል​ቃሉ፤ እሳት ወደ​ቀች፥ ፀሐ​ይ​ንም አላ​የ​ኋ​ትም።


እሾ​ኻ​ችሁ ሳይ​ታ​ወቅ በትር ሆነ፤ ሕያ​ዋን ሳላ​ችሁ በመ​ዓቱ ይው​ጣ​ች​ኋል።


ነፍ​ሴን ተመ​ል​ክ​ተህ ተቤ​ዣት፤ ስለ ጠላ​ቶ​ችም አድ​ነኝ።


አሕ​ዛ​ብም ይዘው ወደ ስፍ​ራ​ቸው ያመ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገ​ኖች ይካ​ፈ​ሏ​ቸ​ዋል፤ በዚ​ያም ሀገር ይበ​ዛሉ፤ በዚ​ያም ወን​ዶች ባሮ​ችና ሴቶች ባሮች ይሆ​ናሉ። ማር​ከው የወ​ሰ​ዷ​ቸ​ውም ለእ​ነ​ርሱ ምር​ኮ​ኞች ይሆ​ናሉ፤ የገ​ዙ​አ​ቸ​ውም ይገ​ዙ​ላ​ቸ​ዋል።


ለሚ​ያ​ዋ​ር​ዱ​አ​ችሁ ወዮ​ላ​ቸው! እና​ን​ተን ግን የሚ​ያ​ዋ​ር​ዳ​ችሁ የለም፤ የሚ​ወ​ነ​ጅ​ላ​ችሁ እና​ን​ተን የሚ​ወ​ነ​ጅል አይ​ደ​ለም፤ ወን​ጀ​ለ​ኞች ይጠ​መ​ዳሉ፤ ይያ​ዛ​ሉም፤ ብል እን​ደ​በ​ላው ልብ​ስም ያል​ቃሉ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ የቍ​ጣ​ውን ጽዋ የጠ​ጣሽ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቁሚ፤ የሚ​ያ​ን​ገ​ደ​ግ​ድ​ሽን የቍ​ጣ​ውን ጽዋ ጠጥ​ተ​ሻ​ልና፥ ጨል​ጠ​ሽ​ው​ማ​ልና።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ የክ​ን​ድ​ሽ​ንም ኀይል ልበሺ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ዘመን እንደ ጥንቱ ትው​ልድ ተነሺ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ብር​ሃ​ንሽ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በአ​ንቺ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና አብሪ፤ አብሪ።


ስለ​ዚህ ነቃሁ፤ ተመ​ለ​ከ​ት​ሁም፤ እን​ቅ​ል​ፌም ጣፈ​ጠኝ።


ለጽ​ድቅ ትጉ፤ አት​ሳቱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ያ​ው​ቁት ሰዎች አሉና፤ ነገር ግን እን​ድ​ታ​ፍሩ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤


“ምር​ኮን ማር​ከህ ወደ ሰማይ ወጣህ፤ ጸጋ​ህ​ንም ለሰው ልጅ ሰጠህ” ይላ​ልና።


“የተ​ኛህ ንቃ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይ​ተህ ተነሥ፤ ክር​ስ​ቶ​ስም ያበ​ራ​ል​ሃል” ብሎ​አ​ልና።


በዚያ ጊዜ የቀ​ሩት ወደ ኀያ​ላ​ኑና ወደ ሕዝቡ ወረዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ እኔ በኀ​ያ​ላን ላይ ወረደ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios