Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መሳፍንት 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሲሣ​ራም፥ “ጠም​ቶ​ኛ​ልና እባ​ክሽ የም​ጠ​ጣው ጥቂት ውኃ ስጪኝ” አላት፤ እር​ስ​ዋም የወ​ተ​ቱን ዕቃ ፈትታ አጠ​ጣ​ችው፤ ፊቱ​ንም ሸፈ​ነ​ችው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሲሣራም፣ “ጠምቶኛልና እባክሽን ውሃ አጠጪኝ” አላት፤ እርሷም የወተት ዕቃውን ከፍታ የሚጠጣውን ሰጠችው፤ እንደ ገናም ሸፈነችው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሲሣራም፥ “ጠምቶኛልና እባክሽን ውሃ አጠጪኝ” አላት፤ እርሷም የወተት ጮጮውን ከፍታ የሚጠጣውን ሰጠችው፤ እንደገናም ሸፈነችው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሲሣራም “እባክሽ የምጠጣው ውሃ ስጪኝ፤ በጣም ጠምቶኛል” አላት፤ እርስዋም ከቈዳ የተሠራውን የወተት ዕቃ ከፍታ አጠጣችውና እንደገና ሸፍና ደበቀችው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እርሱም፦ ጠምቶኛልና እባክሽ የምጠጣው ጥቂት ውኃ ስጭኝ አላት፥ እርስዋም የወተቱን አቁማዳ ፈትታ አጠጣችው፥ ሸፈነችውም።

Ver Capítulo Cópia de




መሳፍንት 4:19
8 Referências Cruzadas  

እነሆ፥ እኔ በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ቆሜ​አ​ለሁ፤ የከ​ተ​ማዋ ሰዎች ሴቶች ልጆ​ችም ውኃን ሊቀዱ ይወ​ጣሉ፤ ጥቂት ውኃ ከእ​ን​ስ​ራሽ አጠ​ጪኝ ስላት፥


ተነ​ሥ​ቶም ወደ ሰራ​ፕታ ሄደ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በር በደ​ረሰ ጊዜ አን​ዲት መበ​ለት በዚያ እን​ጨት ትለ​ቅም ነበር፤ ኤል​ያ​ስም ጠርቶ፥ “የም​ጠ​ጣው ጥቂት ውኃ በጽዋ ታመ​ጭ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሻ​ለሁ” አላት።


ድሆ​ችና ምስ​ኪ​ኖች ውኃ ይሻሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ምም፤ ምላ​ሳ​ቸ​ውም በጥ​ማት ደር​ቋል፤ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እኔ አል​ተ​ዋ​ቸ​ውም።


እነሆ፥ ከሰ​ማ​ርያ አን​ዲት ሴት ውኃ ልት​ቀዳ መጣች፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት።


ኢያ​ዔ​ልም ሲሣ​ራን ለመ​ቀ​በል ወጥታ፥ “ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፤ አት​ፍ​ራም” አለ​ችው። ወደ እር​ስ​ዋም ወደ ድን​ኳ​ንዋ ገባ፤ በም​ን​ጣ​ፍም ሸፈ​ነ​ችው።


እር​ሱም፥ “ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ቁሚ፤ ሰውም መጥቶ፦ ‘በዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠ​ይ​ቅሽ አንቺ፦ ‘የለም’ ትዪ​ዋ​ለሽ” አላት።


የቄ​ና​ዊው የሔ​ቤር ሚስት ኢያ​ዔል፥ ከሴ​ቶች ይልቅ የተ​ባ​ረ​ከች ትሁን፤ በድ​ን​ኳን ውስጥ ከሚ​ኖሩ ሴቶች ይልቅ የተ​ባ​ረ​ከች ትሁን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios