Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መሳፍንት 15:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ “ይህን ያደ​ረገ ማን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም፥ “ሚስ​ቱን ወስዶ ለሚ​ዜው አጋ​ብ​ቶ​በ​ታ​ልና የቴ​ም​ና​ታ​ዊዉ አማች ሶም​ሶን ነው” አሉ​አ​ቸው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወጥ​ተው የአ​ባ​ቷን ቤትና እር​ስ​ዋን አባ​ቷ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ፍልስጥኤማውያን፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ፣ “ሚስቱ ለሚዜው ስለ ተሰጠችበት የተምናዊው ዐማች ሳምሶን ነው” የሚል መልስ አገኙ። ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጥለው ገደሏቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፍልስጥኤማውያን፥ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ፥ “ሚስተ ለሚዜው ስለ ተሰጠችበት የቲምናዊው ዐማች ሳምሶን ነው” የሚል መልስ አገኙ። ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጥለው ገደሏቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ፍልስጥኤማውያን ይህን ያደረገው ማን እንደሆን በጠየቁ ጊዜ፥ ሶምሶን መሆኑን ተረዱ፤ የቲምና ተወላጅ የሆነው ዐማቱ የሶምሶንን ሚስት ሚዜው ለነበረ ሌላ ሰው ሰጥቶበት ነበር፤ ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ሄደው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጠሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ፍልስጥኤማውያንም፦ ይህን ያደረገው ማን ነው? አሉ። እነርሱም፦ ሚስቱን ወስዶ ለሚዜው አጋብቶበታልና የተምናዊው አማች ሶምሶን ነው አሉ። ፍልስጥኤማያንም ወጥተው ሴቲቱንና አባትዋን በእሳት አቃጠሉ።

Ver Capítulo Cópia de




መሳፍንት 15:6
6 Referências Cruzadas  

ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።


አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


የኤ​ፍ​ሬ​ምም ሰዎች ተሰ​በ​ሰቡ፤ ወደ ጻፎ​ንም ተሻ​ግ​ረው ዮፍ​ታ​ሔን፥ “ከአ​ሞን ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ስታ​ልፍ ከአ​ንተ ጋር እን​ድ​ን​ሄድ ስለ​ምን አል​ጠ​ራ​ኸ​ንም? ቤት​ህን በአ​ንተ ላይ በእ​ሳት እና​ቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለን” አሉት።


ከዚህ በኋላ በአ​ራ​ተ​ኛው ቀን የሶ​ም​ሶ​ንን ሚስት፥ “እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን እን​ዲ​ነ​ግ​ርሽ ባል​ሽን አባ​ብ​ይው፤ አለ​ዚ​ያም አን​ቺ​ንና የአ​ባ​ት​ሽን ቤት በእ​ሳት እና​ቃ​ጥ​ላ​ለን፤ ወይስ ወደ​ዚህ የጠ​ራ​ች​ሁን ልታ​ደ​ኸ​ዩን ነውን?” አሉ​አት።


ችቦ​ው​ንም አን​ድዶ በቆ​መው በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እህል መካ​ከል ሰደ​ዳ​ቸው፤ ነዶ​ው​ንም፥ ክም​ሩ​ንም፥ የቆ​መ​ዉ​ንም እህል፥ ወይ​ኑ​ንም፥ ወይ​ራ​ዉ​ንም አቃ​ጠለ።


ሶም​ሶ​ንም አላ​ቸው- “ይህን ብታ​ደ​ር​ጉም ደስ አይ​ለ​ኝም፤ በቀሌ ከአ​ንድ ሰው ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ሁላ​ች​ሁ​ንም እበ​ቀ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ አር​ፋ​ለሁ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios