Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መሳፍንት 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ማኑ​ሄም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወደ እኛ የላ​ክ​ኸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው፥ እባ​ክህ እን​ደ​ገና ወደ እኛ ይምጣ፤ ለሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ልጅ ምን እን​ደ​ም​ና​ደ​ርግ ያስ​ገ​ን​ዝ​በን” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም ማኑሄ፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚወለደውን ልጅ እንዴት አድርገን ማሳደግ አንዳለብን እንዲያስተምረን ያ ወደ እኛ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደ ገና እንዲመጣ ታደርግ ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከዚያም ማኑሄ፥ “ጌታ ሆይ፥ የሚወለደውን ልጅ እንዴት አድርገን ማሳደግ አንዳለብን እንዲያስተምረን ያ ወደኛ የላከው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና እንዲመጣ እለምንሃለሁ” ብሎ ወደ ጌታ ጸለየ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ በኋላ ማኑሄ “እግዚአብሔር ሆይ! ሕፃኑ ሲወለድ ምን ማድረግ እንደሚገባን ይነግረን ዘንድ ያ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና ተመልሶ ወደ እኛ እንዲመጣ አድርግልን” ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ማኑሄም፦ ጌታ ሆይ፥ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው፥ እባክህ፥ እንደ ገና ወደ እኛ ይምጣ፥ ለሚወለደውም ልጅ ምን እንድናደርግ ያስገንዝበን ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ።

Ver Capítulo Cópia de




መሳፍንት 13:8
8 Referências Cruzadas  

እኔ ራሴ አያ​ለሁ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ሠርቼ እንደ ሆነ፥ ሐሰ​ት​ንም ተና​ግሬ እንደ ሆነ፥ ደግሜ እን​ዳ​ል​ሠራ አንተ አሳ​የኝ።


እር​ሱም እየ​ፈ​ራና እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ርግ ትሻ​ለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነ​ሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚ​ያም ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህን ይነ​ግ​ሩ​ሃል” አለው።


ማኑ​ሄም ተነ​ሥቶ ሚስ​ቱን ተከ​ተለ፤ ወደ ሰው​ዬ​ዉም መጥቶ፥ “ከሚ​ስቴ ጋር የተ​ነ​ጋ​ገ​ርህ አንተ ነህን?” አለው። መል​አ​ኩም፥ “እኔ ነኝ” አለ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለሴ​ቲቱ ተገ​ልጦ እን​ዲህ አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ድ​ሽም፤ ነገር ግን ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ።


ሴቲ​ቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መል​ኩም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ነበረ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ መጣ ጠየ​ቅ​ሁት፥ እር​ሱም ስሙን አል​ነ​ገ​ረ​ኝም።


እር​ሱም፦ እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ እን​ግ​ዲህ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥን አት​ጠጪ፥ ርኩስ ነገ​ር​ንም አት​ብዪ፤ ልጁ ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ እስ​ኪ​ሞት ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና አለኝ” ብላ ተና​ገ​ረች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የማ​ኑ​ሄን ቃል ሰማ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ እንደ ገና በእ​ርሻ ውስጥ ተቀ​ምጣ ሳለች ወደ ሴቲቱ መጣ፤ ባልዋ ማኑሄ ግን ከእ​ር​ስዋ ጋር አል​ነ​በ​ረም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios