Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 9:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አሁ​ንም እነሆ፥ በእ​ጃ​ችሁ ውስጥ ነን፤ እንደ ወደ​ዳ​ች​ሁና ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ችሁ አድ​ር​ጉ​ብን” አሉት፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እነሆ፤ አሁን በእጅህ ውስጥ ነን፤ በጎና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ በእጅህ ውስጥ ነን፤ ለዓይንህም መልካምና ቅን የመሰለውን ነገር አድርግብን።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እነሆ፥ አሁን በእናንተ ሥልጣን ሥር ነን፤ መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግብን።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አሁንም፥ እነሆ፥ በእጅህ ውስጥ ነን፥ ለዓይንህም መልካምና ቅን የመሰለውን ነገር አድርግብን አሉት።

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 9:25
12 Referências Cruzadas  

አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራን፥ “እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ይሽ በእ​ጅሽ ናት፤ እንደ ወደ​ድሽ አድ​ር​ጊ​ባት” አላት። ሦራም አጋ​ርን አሠ​ቃ​የ​ቻት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ኰበ​ለ​ለች።


ነገር ግን አል​ወ​ድ​ድ​ህም ቢለኝ፥ እነ​ሆኝ በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ያድ​ር​ግ​ብኝ” አለው።


ዳዊ​ትም ጋድን፥ “በሁ​ሉም እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ በሰው እጅ ከም​ወ​ድቅ ይልቅ ምሕ​ረቱ ብዙ ነውና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ ይሻ​ለ​ኛል” አለው።


የአ​ክ​አ​ብም የቤቱ አለ​ቆች፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹና ልጆ​ቹ​ንም የሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን፤ ያዘ​ዝ​ኸ​ን​ንም ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ የም​ና​ነ​ግ​ሠው ሰው የለም፤ የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አድ​ርግ” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ።


በሕ​ዝቤ ላይ ተቈ​ጥቼ ነበር፤ ርስ​ቴ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ በእ​ጅ​ሽም አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸው አል​ራ​ራ​ሽም፤ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም እጅግ አክ​ብ​ደ​ሻል።


እኔ ግን፥ እነሆ በእ​ጃ​ችሁ ነኝ፤ በዐ​ይ​ና​ችሁ መል​ካ​ምና ቅን የመ​ሰ​ለ​ውን አድ​ር​ጉ​ብኝ።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ “ንጉሡ በእ​ና​ንተ ላይ ምንም ሊያ​ደ​ርግ አይ​ች​ል​ምና እነሆ በእ​ጃ​ችሁ ነው” አለ።


አዎን አባት ሆይ! ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።


ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅ አዳ​ና​ቸው፤ አል​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ው​ምም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እኛ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ናል፤ አንተ በፊ​ትህ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን አድ​ር​ግ​ብን፤ ዛሬ ግን እባ​ክህ አድ​ነን” አሉት።


ጌዴ​ዎ​ንም ወደ ሱኮት አለ​ቆች መጥቶ፥ “ለደ​ከ​ሙት ሰዎ​ችህ እህል እን​ሰጥ ዘንድ የዛ​ብ​ሄ​ልና የስ​ል​ማና እጅ አሁን በእ​ጅህ ነውን? ብላ​ችሁ የተ​ላ​ገ​ዳ​ች​ሁ​ብኝ፥ ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማና እነሆ፥” አለ።


ሳሙ​ኤ​ልም ነገ​ሩን ሁሉ ነገ​ረው፤ አን​ዳ​ችም አል​ሸ​ሸ​ገ​ውም። ዔሊም፥ “እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ደስ ያሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ” አለ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios