Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 4:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እስ​ክ​ና​ልፍ ድረስ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ከፊ​ታ​ችን እን​ዳ​ደ​ረቀ እን​ዲሁ እስ​ክ​ን​ሻ​ገር ድረስ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ ከፊ​ታ​ችን አደ​ረቀ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እኛ እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቀይ ባሕርን እንዳደረቀው ሁሉ፣ እናንተም እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ወንዝ በፊታችሁ አደረቀው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ ጌታ የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አምላካችን እግዚአብሔር እስክንሻገር ድረስ አስቀድሞ ለእኛ የቀይ ባሕርን እንዳደረቀልን፥ ለእናንተም የዮርዳኖስን ወንዝ እስክትሻገሩ ድረስ ውሃ አድርቆ ያሻገራችሁ መሆኑን ንገሩአቸው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 4:23
8 Referências Cruzadas  

አንተ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዝብ ሁሉ ስም​ህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝ​ብህ እንደ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ሩህ ዘንድ፥ በዚ​ህም በሠ​ራ​ሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እን​ግ​ዳው የሚ​ለ​ም​ን​ህን ሁሉ አድ​ርግ።


ከፊ​ታ​ቸ​ውም ባሕ​ሩን ከፈ​ልህ፤ በባ​ሕ​ሩም መካ​ከል በደ​ረቅ ዐለፉ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውን ግን ድን​ጋይ በጥ​ልቅ ውኃ እን​ዲ​ጣል በቀ​ላይ ውስጥ ጣል​ሃ​ቸው።


እኛ ሕዝ​ብህ ግን፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ህም በጎች፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እና​መ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለን፤ ለልጅ ልጅም ምስ​ጋ​ና​ህን እን​ና​ገ​ራ​ለን።


ሙሴም በባ​ሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሌሊ​ቱን ሁሉ ጽኑ የአ​ዜብ ነፋስ አም​ጥቶ ባሕ​ሩን አስ​ወ​ገ​ደው፤ ባሕ​ሩ​ንም አደ​ረ​ቀው፤ ውኃ​ውም ተከ​ፈለ።


“የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶች ከሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹና ከፈ​ረ​ሰ​ኞቹ ጋር ወደ ባሕር ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የባ​ሕ​ሩን ውኆች መለ​ሰ​ባ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ አለፉ፤ ውኃ​ውም ለእ​ነ​ርሱ በቀኝ እንደ ግድ​ግዳ፥ በግ​ራም እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።”


በባ​ሕር ውስጥ መን​ገ​ድን በኀ​ይ​ለ​ኛም ውኃ ውስጥ መተ​ላ​ለ​ፊ​ያን ያደ​ረገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፦


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios