Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 21:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ከጋ​ድም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ራሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃሚ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ከጋድ ነገድ፣ በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንና መሰማሪያዋን፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ከጋድ ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞት፥ ማሕናይም፥

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰምርያዋን፥ መሃናይምንና መሰምርያዋን፥

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 21:38
14 Referências Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም በአ​ያ​ቸው ጊዜ፥ “እነ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ናቸው” አለ፤ የዚ​ያ​ንም ስፍራ ስም “ተዓ​ይን” ብሎ ጠራው።


ዳዊ​ትም ወደ ምና​ሄም መጣ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ ከእ​ርሱ ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ።


ቤር​ዜ​ሊም እጅግ ያረጀ የሰ​ማ​ንያ ዓመት ሽማ​ግሌ ነበረ፤ እጅ​ግም ትልቅ ሰው ነበ​ረና ንጉሡ በመ​ና​ሄም ሳለ ይቀ​ል​በው ነበር።


የሳ​ኦ​ልም ጭፍራ አለቃ የኔር ልጅ አበ​ኔር የሳ​ኦ​ልን ልጅ ኢያ​ቡ​ስ​ቴን ወስዶ ከሰ​ፈር ወደ መሃ​ና​ይም አወ​ጣው፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ የእኛ እንደ ሆነች፥ እኛም ከሶ​ርያ ንጉሥ እጅ ሳን​ወ​ስ​ዳት ዝም እን​ዳ​ልን ታው​ቃ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው።


በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤


በማ​ሃ​ና​ይም የሳዶ ልጅ አሒ​ና​ዳብ ነበረ፤


ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ያለ​ችው ሬማ​ትና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ መሃ​ና​ይ​ምና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፤


ለሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳ በደ​ል​ዳላ ስፍራ ያለ ባሶር፥ ለጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ያለ ራሞት፥ ለም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ያለ ጎላን ነበሩ።


ከሐ​ሴ​ቦን ጀምሮ እስከ አራ​ቦት መሴፋ፥ እስከ ቦጣ​ኒም ድረስ፥ ከማ​ኦን ጀምሮ እስከ ዴቦን ዳርቻ ድረስ፥


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከመ​ሐ​ና​ይም ጀምሮ የባ​ሳን ንጉሥ የዐግ መን​ግ​ሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባ​ሳ​ንም ያሉት የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ሁሉ ስድ​ሳው ከተ​ሞች፥ የገ​ለ​ዓ​ድም እኩ​ሌታ፥


በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ከኢ​ያ​ሪኮ ወደ ምሥ​ራቅ ከሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳው በደ​ል​ዳ​ላው ስፍራ ቦሶ​ርን፥ ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ኤር​ሞ​ትን፥ ከም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ጎላ​ንን ለዩ።


ቄዴ​ሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ሜፍ​ዐ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ።


ሐሴ​ቦ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios