Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 19:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ከዚ​ያም ወደ ኤብ​ሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ አሜ​ማ​ህን፥ ወደ ቀን​ታን እስከ ታላቁ ሲዶና ይደ​ር​ሳል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በመቀጠልም ወደ ዔብሮን፣ ወደ ረአብ፣ እንዲሁም ወደ ሐሞንና ወደ ቃና ሽቅብ ወጥቶ እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲዶናም ደረሰ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ወደ ዔብሮን፥ ረሖብ፥ ሐሞንና ቃና አልፎ እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረአብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲዶናም ደረሰ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 19:28
15 Referências Cruzadas  

የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ወሰን ከሲ​ዶን እስከ ጌራ​ራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶ​ምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳ​ማና ወደ ሴባ​ዮም እስከ ላሳ ይደ​ር​ሳል።


ወደ ገለ​ዓ​ድም አዳ​ሳይ ወደ​ም​ት​ባል ወደ ተባ​ሶን ሀገ​ርም መጡ፤ ወደ ዳኒ​ዳ​ንና ወደ ኡዳ​ንም ደረሱ፤ ወደ ሲዶ​ናም ዞሩ፤


ወደ ጤሮ​ስም ምሽግ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ከተ​ሞች ሁሉ መጡ፤ በይ​ሁ​ዳም ደቡብ በኩል በቤ​ር​ሳ​ቤህ ወጡ።


እር​ሱም፥ “አንቺ የተ​በ​ደ​ልሽ የሲ​ዶና ድን​ግል ልጅ ሆይ፥ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ደስ አይ​በ​ልሽ፤ ተነ​ሥ​ተሽ ወደ ኪቲም ተሻ​ገሪ፤ በዚ​ያም ደግሞ አታ​ር​ፊም” አለ።


በደ​ሴት የሚ​ኖሩ በባ​ሕር የሚ​ሻ​ገሩ የፊ​ኒቄ ስደ​ተ​ኞች ምን ይመ​ስ​ላሉ?


ሲዶና ሆይ፥ ባሕር፥ የባ​ሕር ምሽግ፥ “አላ​ማ​ጥ​ሁም፥ አል​ወ​ለ​ድ​ሁም፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ት​ንም አላ​ሳ​ደ​ግ​ሁም፥ ደና​ግ​ል​ንም አላ​ሳ​ደ​ግ​ሁም” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እፈሪ።


የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ሲዶና አቅ​ን​ተህ ትን​ቢት ተና​ገ​ር​ባት፤ እን​ዲ​ህም በል፦


በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የገ​ሊላ ክፍል በም​ት​ሆን በቃና ሰርግ ሆነ፤ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ እና​ትም በዚያ ነበ​ረች።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ውኃ​ውን የወ​ይን ጠጅ ወደ አደ​ረ​ገ​በት የገ​ሊላ ክፍል ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ቃና ዳግ​መኛ ሄደ። በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ልጁ የታ​መ​መ​በት የን​ጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤


በማ​ግ​ሥ​ቱም ወደ ሲዶና ደረ​ስን፤ ዩል​ዮ​ስም ለጳ​ው​ሎስ አዘ​ነ​ለት፤ ወደ ወዳ​ጆቹ እን​ዲ​ሄ​ድና በእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ር​ፍም ፈቀ​ደ​ለት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ መቱ​አ​ቸ​ውም፤ ወደ ታላ​ቂ​ቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴ​ሮ​ንም፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወዳ​ለው ወደ ሞሳሕ ሸለቆ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ማን​ንም ሳያ​ስ​ቀሩ መቱ​አ​ቸው።


ሔል​ቃ​ት​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ረዓ​ብ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱ​ንም ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።


አሴ​ርም የዓኮ ነዋ​ሪ​ዎ​ችን አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ገባ​ሮች ሆኑ​ላ​ቸው፤ የዶር ነዋ​ሪ​ዎ​ች​ንና የሲ​ዶን ነዋ​ሪ​ዎ​ችን፥ የደ​ላ​ፍ​ንም ነዋ​ሪ​ዎች፥ የአ​ክ​ሶ​ዚ​ብ​ንና የሄ​ል​ባን፥ የአ​ፌ​ቅ​ንና የረ​ዓ​ብ​ንም ሰዎች አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም።


የሚ​ታ​ደ​ግም አል​ነ​በ​ረም፤ ከሲ​ዶና ርቀው ነበ​ርና፥ እነ​ር​ሱም ከሌ​ሎች ሰዎች ጋር ግን​ኙ​ነት አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ው​ምና። እር​ስ​ዋም በቤ​ት​ሮ​አብ አጠ​ገብ ባለች ሸለቆ ውስጥ ነበ​ረች፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሠር​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios