Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 18:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎ​ችን አምጡ፥ ተነ​ሥ​ተ​ውም ሀገ​ሪ​ቱን ይዙ​ሩ​አት፤ ለመ​ክ​ፈ​ልም እን​ዲ​ያ​መች ገል​ጠው ይጻ​ፉ​አት፤ ወደ እኔም ይመ​ለ​ሳሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አሁንም ከእያንዳንዱ ነገድ ሦስት ሦስት ሰው ምረጡ፤ እኔም ምድሪቱን ተዘዋውረው እንዲያጠኑና እያንዳንዱም ነገድ መውረስ የሚገባውን ድርሻ ዝርዝር መግለጫ ጽፈው እንዲያመጡ እልካቸዋለሁ፤ ከዚያም ወደ እኔ ይመለሳሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከየነገዱ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ፤ ተነሥተውም አገሩን ይዞራሉ፥ እንደ ርስታቸውም መጠን ይመዘግቡታል፤ ከዚያም በኋላ ወደ እኔ ይመለሳሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከእያንዳንዱ ነገድ ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡልኝ፤ እኔም እያንዳንዱ ነገድ ማግኘት የሚገባውን የርስት ድርሻ ለማወቅ የምድሪቱን ሁኔታ አጥንተው እንዲመዘግቡ በመላ አገሪቱ እልካቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው ወደ እኔ ይመጣሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከየነገዱ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ፥ ተነሥተውም አገሩን ይዞራሉ፥ እንደ ርስታቸውም መጠን ይጽፉታል፥ ወደ እኔም ይመለሳሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 18:4
9 Referências Cruzadas  

ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ መካከል በዕጣ ገመድ የሚጥል አይኖርህም።


እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ከየ​ነ​ገዱ አለ​ቆች አንድ አንድ ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን።


“ይገ​ዙ​አት ዘንድ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የም​ሰ​ጣ​ትን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር የሚ​ሰ​ልሉ ሰዎ​ችን ላክ፤ ከአ​ባ​ቶች ቤት ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነገድ ሁሉ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አለቃ የሆነ አንድ አንድ ሰው ትል​ካ​ላ​ችሁ።”


ኢያ​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አላ​ቸው፥ “የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጣ​ች​ሁን ምድር እን​ዳ​ት​ወ​ር​ሱ​አት እስከ መቼ ድረስ ታቈ​ዩ​አ​ታ​ላ​ችሁ?


በሰ​ባ​ትም ክፍል ይከ​ፍ​ሉ​ታል፤ ይሁዳ በደ​ቡብ በኩል በዳ​ር​ቻው ውስጥ ይቀ​መ​ጣል፤ የዮ​ሴ​ፍም ልጆች በሰ​ሜን በኩል በዳ​ር​ቻው ውስጥ ይቀ​መ​ጣሉ።


እና​ን​ተም ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ባት ክፍል ክፈ​ሏት፤ ወደ እኔም ወዲህ አም​ጡ​ልኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ሰዎ​ቹም ሄደው ምድ​ሩን ዞሩ፥ አዩ​ትም፤ እንደ ከተ​ሞ​ችም በሰ​ባት ክፍል ከፈ​ሉት፤ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ጻፉት፤ ወደ ኢያ​ሱም አመጡ።


አሁ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን።


“ከሕ​ዝቡ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን ውሰድ፦


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios