Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 15:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የካ​ሌብ ወን​ድም የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያል ያዛት፤ ልጁን አክ​ሳ​ንም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዛት፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፤ ስለዚህ ካሌብ ልጁን ዓክሳንን አጋባው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህም የካሌብ ወንድም ከሆነው ከቀናዝ የተወለደው ዖትኒኤል ያችን ከተማ ወግቶ ያዘ፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፥ ልጁንም ዓክሳን አጋባው።

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 15:17
9 Referências Cruzadas  

ደግ​ሞም የም​ድ​ሜ​ናን አባት ስጋ​ብን የመ​ክ​ቢ​ና​ንና የጌ​ባ​ልን አባት ሳዑ​ልን ወለ​ደች፤ የካ​ሌ​ብም ሴት ልጅ አስካ ነበ​ረች።


በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ዐሥራ ሁለ​ተ​ኛው አለቃ ከጎ​ቶ​ን​ያል ወገን የነ​በ​ረው ነጦ​ፋ​ታ​ዊው ኬል​ዳይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።


የቄ​ኔ​ዝም ልጆች ጎቶ​ን​ያ​ልና ሠራ​ኢያ ነበሩ። የጎ​ቶ​ን​ያ​ልም ልጅ አታት ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ዚህ፥ ልዩ ከሆነ ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር፤


የይ​ሁ​ዳም ልጆች በጌ​ል​ገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔ​ዛ​ዊ​ውም የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፥ “ለአ​ም​ላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃ​ዴስ በርኔ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታው​ቃ​ለህ።


ካሌ​ብም፥ “ሀገረ መጻ​ሕ​ፍ​ትን ለሚ​መታ፥ ለሚ​ይ​ዛ​ትም ልጄን አክ​ሳን ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ” አለ።


የካ​ሌ​ብም ትንሽ ወን​ድም የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያል ያዛት፤ ሚስ​ትም ትሆ​ነው ዘንድ ልጁን ዓስ​ካን ሰጠው።


ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ዐረ​ፈች፤ የቄ​ኔ​ዝም ልጅ ጎቶ​ን​ያል ሞተ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል መድ​ኀ​ኒ​ትን አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው። የካ​ሌብ የታ​ናሽ ወን​ድሙ የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያ​ልም አዳ​ና​ቸው፤ ለእ​ር​ሱም ታዘ​ዙ​ለት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios