Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 6:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው በቀር አብን ያየው ማንም የለም፤ እር​ሱም አብን አየው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሆነው በቀር አብን ያየ ማንም የለም፤ አብን ያየው እርሱ ብቻ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 አብን ያየ ማንም የለም፤ ከእግዚአብሔር ከሆነው በቀር፥ እርሱ አብን አይቶአል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ይህም ማለት አብን ያየው ሰው አለ ማለት አይደለም፤ አብን ያየው ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣው እርሱ ብቻ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 አብን ያየ ማንም የለም፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር፥ እርሱ አብን አይቶአል።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 6:46
14 Referências Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የቆ​መ​በ​ትን ቦታ አዩ፤ ከእ​ግ​ሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚ​ያ​በራ፥ እንደ ብሩህ ሰን​ፔር ድን​ጋይ የሚ​መ​ስል ወለል ነበረ።


ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።


ሁሉ ከአ​ባቴ ዘንድ ተሰ​ጠኝ፤ ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ አብም ማን እንደ ሆነ ከወ​ልድ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም። ወልድ ግን ለወ​ደ​ደው ይገ​ል​ጥ​ለ​ታል።”


በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።


እኔ​ንስ ብታ​ው​ቁኝ አባ​ቴ​ንም ባወ​ቃ​ች​ሁት ነበር፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን አው​ቃ​ች​ሁ​ታል፤ አይ​ታ​ች​ሁ​ት​ማል።”


ሌላ ያል​ሠ​ራ​ውን ሥራ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ባል​ሠራ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን እኔ​ንም አባ​ቴ​ንም አይ​ተ​ዋል፤ ጠል​ተ​ው​ማል።


የላ​ከኝ አብም ስለ እኔ መስ​ክ​ሮ​አል፤ ከሆ​ነም ጀምሮ ቃሉን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ መል​ኩ​ንም አላ​ያ​ች​ሁም።


እኔ ግን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ እኔ ከእ​ርሱ ነኝና፥ እር​ሱም ልኮ​ኛ​ልና።


እነ​ር​ሱም፥ “አባ​ትህ የት ነው?” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔን አታ​ው​ቁም፤ አባ​ቴ​ንም አታ​ው​ቁም፤ እኔ​ንስ ብታ​ውቁ አባ​ቴ​ንም ባወ​ቃ​ች​ሁት ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።


እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ እኔ ግን ኣው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ አላ​ው​ቀ​ውም ብልም እንደ እና​ንተ ሐሰ​ተኛ እሆ​ና​ለሁ፤ እኔ አው​ቀ​ዋ​ለሁ ቃሉ​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ።


ይኸ​ውም የማ​ይ​ታይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው፥ ከፍ​ጥ​ረቱ ሁሉ በላይ የሆነ በኵር ነው።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።


እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios