Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 5:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ሙሴ​ንስ አም​ና​ች​ሁት ቢሆን እኔ​ንም ባመ​ና​ች​ሁኝ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎ​አ​ልና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ሙሴን ብታምኑ ኖሮ፣ እኔን ባመናችሁ ነበር፤ ምክንያቱም እርሱ የጻፈው ስለ እኔ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ሙሴንስ ብታምኑት እኔንም ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ሙሴን ብታምኑ ኖሮ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና እኔንም ባመናችሁ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 5:46
21 Referências Cruzadas  

የሚ​ረ​ግ​ሙ​ህ​ንም እረ​ግ​ማ​ለሁ፤ የም​ድር ነገ​ዶ​ችም ሁሉ በአ​ንተ ይባ​ረ​ካሉ።”


አብ​ር​ሃም በእ​ው​ነት ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆ​ና​ልና፤ የም​ድር ሕዝ​ቦ​ችም ሁሉ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካ​ሉና።


የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉም በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤ ቃሌን ሰም​ተ​ሃ​ልና።”


ዘር​ህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እስከ ባሕ​ርና እስከ አዜብ እስከ መስ​ዕና እስከ ምሥ​ራቅ ይበ​ዛል፤ ይሞ​ላ​ልም፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በአ​ንተ፥ በዘ​ር​ህም ይባ​ረ​ካሉ።


በአ​ን​ተና በሴ​ቲቱ መካ​ከል፥ በዘ​ር​ህና በዘ​ር​ዋም መካ​ከል ጠላ​ት​ነ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እርሱ ራስ​ህን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፤ አን​ተም ሰኰ​ና​ውን ትነ​ድ​ፋ​ለህ።”


መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


እር​ሱም ከሙ​ሴና ከነ​ቢ​ያት፥ ከመ​ጻ​ሕ​ፍ​ትም ሁሉ ስለ እርሱ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን ይተ​ረ​ጕ​ም​ላ​ቸው ጀመር።


ፊል​ጶስ ግን ከእ​ን​ድ​ር​ያ​ስና ከጴ​ጥ​ሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበር።


ሙሴ የጻ​ፈ​ውን ካላ​መ​ና​ችሁ ግን የእ​ኔን ቃል እን​ዴት ታም​ና​ላ​ችሁ?”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነ​ኝና ለታ​ላ​ቁም፥ ለታ​ና​ሹም እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ እስከ ዛሬ ደረ​ስሁ፤ ይደ​ረግ ዘንድ ካለው፥ ነቢ​ያት ከተ​ና​ገ​ሩት፥ ሙሴም ከተ​ና​ገ​ረው ሌላ ያስ​ተ​ማ​ር​ሁት የለም።


የኦ​ሪት ጽድቅ ፍጻ​ሜስ ለሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ ማመን ነው።


እኔስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያው ሆኜ በሁ​ለ​ተ​ኛው ሕግ እኖር ዘንድ ከቀ​ደ​መው ሕግ ተለ​የሁ።


በኦ​ሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእ​ር​ግ​ማን ውስጥ ይኖ​ራሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በዚህ በኦ​ሪት መጽ​ሐፍ ውስጥ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ የማ​ይ​ፈ​ጽ​ምና የማ​ይ​ጠ​ብቅ ርጉም ይሁን።”


እኛ​ንስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እኛ የኦ​ሪ​ትን መር​ገም በመ​ሸ​ከሙ ከኦ​ሪት መር​ገም ዋጅ​ቶ​ናል፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በእ​ን​ጨት ላይ የተ​ሰ​ቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”


እን​ግ​ዲህ ኦሪት በእ​ርሱ በማ​መን እን​ጸ​ድቅ ዘንድ ወደ ክር​ስ​ቶስ መሪ ሆነ​ችን።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስ​ነ​ሣ​ል​ሃል፤ እር​ሱ​ንም ስሙት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios