Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እን​ዳ​ል​ጠማ፥ ዳግ​መ​ኛም ውኃ ልቀዳ ወደ​ዚህ እን​ዳ​ል​መጣ እባ​ክህ ከዚህ ውኃ ስጠኝ፤” አለ​ችው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሴትዮዋም፣ “ጌታዬ፤ እንዳልጠማና ውሃ ለመቅዳት እንዳልመላለስ፣ እባክህ ይህን ውሃ ስጠኝ” አለችው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሴቲቱ “ጌታ ሆይ! እንዳልጠማ ውሃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውሃ ስጠኝ፤” አለችው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሴትዮዋም “ጌታ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ውሃ እንዳይጠማኝና ወደዚህም ለመቅዳት እንዳልመጣ እባክህ እንዲህ ዐይነቱን ውሃ ስጠኝ!” አለችው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ አለችው።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 4:15
11 Referências Cruzadas  

“በጎ​ውን ማን ያሳ​የ​ናል?” የሚሉ ብዙ​ዎች ናቸው። አቤቱ፥ የፊ​ትህ ብር​ሃን በላ​ያ​ችን ታወቀ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሂደሽ ባል​ሽን ጥሪና ወደ​ዚህ ነይ” አላት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንተ የም​ት​ፈ​ል​ጉኝ እን​ጀራ ስለ በላ​ች​ሁና ስለ ጠገ​ባ​ችሁ ነው እንጂ ተአ​ም​ራት ስለ አያ​ችሁ አይ​ደ​ለም።


እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ ከዚያ እን​ጀራ ሁል​ጊዜ ስጠን” አሉት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሕ​ይ​ወት እን​ጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚ​መጣ ከቶ አይ​ራ​ብም፤ በእኔ የሚ​ያ​ም​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም።


የኀ​ጢ​አት ትር​ፍዋ ሞት ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ነው።


እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚ​ኖሩ የሥ​ጋን ነገር ያስ​ባ​ሉና፤ እንደ መን​ፈስ ፈቃድ የሚ​ኖሩ ግን የመ​ን​ፈ​ስን ነገር ያስ​ባሉ።


ለሥ​ጋዊ ሰው ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነገር ሞኝ​ነት ይመ​ስ​ለ​ዋ​ልና፥ አይ​ቀ​በ​ለ​ውም፤ በመ​ን​ፈ​ስም የሚ​መ​ረ​መር ስለ​ሆነ ሊያ​ውቅ አይ​ች​ልም።


ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios